1እንዲህም፡ኾነ፤ቅጥሩ፡ከተሠራ፡በዃላ፥ሳንቃዎቹንም፡ካቆምኹ፡በዃላ፥በረኛዎቹና፡መዘምራኑ፡ ሌዋውያኑም፡ከተሾሙ፡በዃላ፥
2ወንድሜን፡ዐናኒንና፡የግንቡን፡አለቃ፡ሐናንያን፡በኢየሩሳሌም፡ላይ፡ሾምዃቸው፤ርሱም፡እውነተኛ፡ ከሌላዎቹም፡ይልቅ፡እግዚአብሔርን፡የሚፈራ፡ሰው፡ነበረ።
3እኔም፦ፀሓይ፡እስኪሞቅ፡ድረስ፡የኢየሩሳሌም፡በሮች፡አይከፈቱ፤እነርሱም፡ቆመው፡ሳሉ፡ደጆቹን፡ ይዝጉ፥ይቈልፉም፤ከኢየሩሳሌምም፡ሰዎች፡አንዳንዱን፡በየተራው፡አንዳንዱንም፡በየቤቱ፡አንጻር፡ጠባቂዎችን፡ አስቀምጡ፡አልዃቸው።
4ከተማዪቱም፡ሰፊና፡ታላቅ፡ነበረች፤በውስጧ፡የነበሩ፡ሕዝብ፡ግን፡ጥቂቶች፡ነበሩ፥ቤቶቹም፡አልተሠሩም፡ ነበር።
5አምላኬም፡ታላቆቹንና፡ሹማምቱን፡ሕዝቡንም፡ሰብስቤ፡እቈጥራቸው፡ዘንድ፡በልቤ፡አደረገ፤አስቀድመው፡ የመጡትን፡ሰዎች፡የትውልድ፡መጽሐፋቸውን፡አገኘኹ፥በርሱም፡እንደዚህ፡ተጽፎ፡አገኘኹ።
6የባቢሎን፡ንጉሥ፡ናቡከደነጾር፡ከማረካቸው፡ምርኮኛዎች፡ወደ፡ኢየሩሳሌምና፡ወደ፡ይሁዳ፡ወደ፡ እየከተማቸው፡የተመለሱት፡የአገር፡ልጆች፡እነዚህ፡ናቸው።
7ከዘሩባቤል፥ከኢያሱ፥ከነሐምያ፥ከዐዛርያስ፥ከረዓምያ፥ከነሐማኒ፥ከመርዶክዮስ፥ከበላሳን፥ከሚስጴሬት፥ከበጉ ዋይ፥ከነሑም፥ከበዓና፡ጋራ፡መጡ።
8የእስራኤልም፡ሕዝብ፡ሰዎች፡ቍጥር፡ይህ፡ነው፤የፋሮስ፡ልጆች፥ኹለት፡ሺሕ፡መቶ፡ሰባ፡ኹለት።
9የሰፋጥያስ፡ልጆች፡ሦስት፡መቶ፡ሰባ፡ኹለት።
10የኤራ፡ልጆች፥ስድስት፡መቶ፡ዐምሳ፡ኹለት።
11ከኢያሱና፡ከኢዮአብ፡ልጆች፡የኾኑ፡የፈሐት፡ሞዐብ፡ልጆች፥ኹለት፡ሺሕ፡ስምንት፡መቶ፡ዐሥራ፡ ስምንት።
12የዔላም፡ልጆች፥ሺሕ፡ኹለት፡መቶ፡ዐምሳ፡አራት።
13የዛቱዕ፡ልጆች፥ስምንት፡መቶ፡አርባ፡ዐምስት።
14የዘካይ፡ልጆች፥ሰባት፡መቶ፡ስድሳ።
15የቢንዊ፡ልጆች፥ስድስት፡መቶ፡አርባ፡ስምንት።
16የቤባይ፡ልጆች፥ስድስት፡መቶ፡ኻያ፡ስምንት።
17የዓዝጋድ፡ልጆች፥ኹለት፡ሺሕ፡ሦስት፡መቶ፡ኻያ፡ኹለት።
18የአዶኒቃም፡ልጆች፥ስድስት፡መቶ፡ስድሳ፡ሰባት።
19የበጉዋይ፡ልጆች፥ኹለት፡ሺሕ፡ስድሳ፡ሰባት።
20የዓዲን፡ልጆች፥ስድስት፡መቶ፡ዐምሳ፡ዐምስት።
21የሕዝቅያስ፡ወገን፡የአጤር፡ልጆች፥ዘጠና፡ስምንት።
22የሐሱም፡ልጆች፥ሦስት፡መቶ፡ኻያ፡ስምንት።
23የቤሳይ፡ልጆች፥ሦስት፡መቶ፡ኻያ፡አራት።
24የሐሪፍ፡ልጆች፥መቶ፡ዐሥራ፡ኹለት።
25የገባዖን፡ልጆች፥ዘጠና፡ዐምስት። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
26የቤተ፡ልሔምና፡የነጦፋ፡ሰዎች፥መቶ፡ሰማንያ፡ስምንት።
27የዓናቶች፡ሰዎች፥መቶ፡ኻያ፡ስምንት።
28የቤትዓዝሞት፡ሰዎች፥አርባ፡ኹለት።
29የቂርያትይዓሪምና፡የከፊራ፡የብኤሮትም፡ሰዎች፥ሰባት፡መቶ፡አርባ፡ሦስት።
30የራማና፡የጌባ፡ሰዎች፥ስድስት፡መቶ፡ኻያ፡አንድ።
31የማክማስ፡ሰዎች፥መቶ፡ኻያ፡ኹለት።
32የቤቴልና፡የጋይ፡ሰዎች፥መቶ፡ኻያ፡ሦስት።
33የኹለተኛው፡ናባው፡ሰዎች፥ዐምሳ፡ኹለት።
34የኹለተኛው፡ዔላም፡ልጆች፥ሺሕ፡ኹለት፡መቶ፡ዐምሳ፡አራት።
35የካሪም፡ልጆች፥ሦስት፡መቶ፡ኻያ።
36የኢያሪኮ፡ልጆች፥ሦስት፡መቶ፡አርባ፡ዐምስት፡
37የሎድና፡የሐዲድ፡የኦኖም፡ልጆች፥ሰባት፡መቶ፡ኻያ፡አንድ።
38የሴናዓ፡ልጆች፥ሦስት፡ሺሕ፡ዘጠኝ፡መቶ፡ሠላሳ።
39ካህናቱ፤ከኢያሱ፡ወገን፡የዮዳዔ፡ልጆች፥ዘጠኝ፡መቶ፡ሰባ፡ሦስት።
40የኢሜር፡ልጆች፥ሺሕ፡ዐምሳ፡ኹለት።
41የፋስኮር፡ልጆች፥ሺሕ፡ኹለት፡መቶ፡አርባ፡ሰባት።
42የካሪም፡ልጆች፥ሺሕ፡ዐሥራ፡ሰባት።
43ሌዋውያኑ፤ከሆዳይዋ፡ወገን፡የኢያሱና፡የቀድምኤል፡ልጆች፥ሰባ፡አራት።
44መዘምራኑ፤የአሣፍ፡ልጆች፥መቶ፡አርባ፡ስምንት።
45በረኛዎቹ፤የሰሎም፡ልጆች፥የአጤር፡ልጆች፥የጤልሞን፡ልጆች፥የዐቁብ፡ልጆች፥የሐጢጣ፡ ልጆች፥የሶባይ፡ልጆች፥መቶ፡ሠላሳ፡ስምንት።
46ናታኒም፥የሲሐ፡ልጆች፥የሐሡፋ፡ልጆች፥
47የጠብዖት፡ልጆች፥የኬራስ፡ልጆች፥የሲዓ፡ልጆች፥
48የፋዶን፡ልጆች፥የልባና፡ልጆች፥
49የአጋባ፡ልጆች፥የሰምላይ፡ልጆች፥የሐናን፡ልጆች፥የጌዴል፡ልጆች፥የጋሐር፡ልጆች፥
50የራያ፡ልጆች፥የረአሶን፡ልጆች፥የኔቆዳ፡ልጆች፥
51የጋሴም፡ልጆች፥የዖዛ፡ልጆች፥የፋሴሐ፡ልጆች፥
52የቤሳይ፡ልጆች፥የምዑናውያን፡ልጆች፥
53የንፉሰሲም፡ልጆች፥የበቅቡቅ፡ልጆች፥የሐቀፋ፡ልጆች፥የሐርሑር፡ልጆች፥
54የበስሎት፡ልጆች፥የምሒዳ፡ልጆች፥የሐርሻ፡ልጆች፥
55የበርቆስ፡ልጆች፥የሢሣራ፡ልጆች፥
56የቴማ፡ልጆች፥የንስያ፡ልጆች፥የሐጢፋ፡ልጆች።
57የሰሎሞን፡ባሪያዎች፡ልጆች፤የሶጣይ፡ልጆች፥የሶፌሬት፡ልጆች፥የፍሩዳ፡ልጆች፥ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
58የየዕላ፡ልጆች፥የደርቆን፡ልጆች፥የጌዴል፡ልጆች፥
59የሰፋጥያስ፡ልጆች፥የሐጢል፡ልጆች፥የፈከራት፡ልጆች፥የሐፂቦይም፡ልጆች፥የዐሞን፡ልጆች።
60ናታኒም፡ዅሉና፡የሰሎሞን፡ባሪያዎች፡ልጆች፡ሦስት፡መቶ፡ዘጠና፡ኹለት፡ነበሩ።
61ከቴልሜላ፥ከቴላሬሳ፥ከክሩብ፥ከአዳን፥ከኢሜር፡የወጡ፡እነዚህ፡ናቸው፤ነገር፡ግን፥የአባቶቻቸውን፡ ቤቶችና፡ዘራቸውን፡ወይም፡ከእስራኤል፡ወገን፡መኾናቸውን፡ያስታውቁ፡ዘንድ፡አልቻሉም፤
62የዳላያ፡ልጆች፥የጦብያ፡ልጆች፥የኔቆዳ፡ልጆች፥ስድስት፡መቶ፡አርባ፡ኹለት።
63ከካህናቱም፡የኤብያ፡ልጆች፥የአቆስ፡ልጆች፥ከገለዓዳዊው፡ከቤርዜሊ፡ልጆች፡ሚስት፡ያገባ፡በስሙም፡ የተጠራ፡የቤርዜሊ፡ልጆች።
64እነዚህ፡በትውልድ፡መጽሐፍ፡ትውልዳቸውን፡ፈለጉ፥ነገር፡ግን፥አልተገኘም፤ከክህነትም፡ተከለከሉ።
65ሐቴርሰታም፦በኡሪምና፡በቱሚም፡የሚፈርድ፡ካህን፡እስኪነሣ፡ድረስ፥ከተቀደሰው፡ነገር፡አትበሉም፡ አላቸው።
67ሰባት፡ሺሕ፡ሦስት፡መቶ፡ሠላሳ፡ሰባት፡ከነበሩ፡ከሎሌዎቻቸውና፡ከገረዶቻቸው፡ሌላ፡ጉባኤው፡ ዅሉ፡አርባ፡ኹለት፡ሺሕ፡ሦስት፡መቶ፡ስድሳ፡ነበሩ፤ኹለቱ፡መቶም፡አርባ፡ዐምስት፡ወንዶችና፡ሴቶች፡ መዘምራን፡ነበሯቸው።
68ፈረሶቻቸውም፡ሰባት፡መቶ፡ሠላሳ፡ስድስት፥በቅሎዎቻቸውም፡ኹለት፡መቶ፡አርባ፡ዐምስት፥
69ግመሎቻቸውም፡አራት፡መቶ፡ሠላሳ፡ዐምስት፥አህያዎቻቸውም፡ስድስት፡ሺሕ፡ሰባት፡መቶ፡ኻያ፡ነበሩ።
70ከአባቶች፡ቤቶች፡አለቃዎችም፡ዐያሌዎቹ፡ሰዎች፡ስለ፡ሥራው፡ስጦታ፡ሰጡ።ሐቴርሰታም፡አንድ፡ሺሕ፡ የወርቅ፡ዳሪክ፥ዐምሳም፡ድስቶች፥ዐምስት፡መቶ፡ሠላሳም፡የካህናት፡ልብስ፡በቤተ፡መዛግብት፡ውስጥ፡ሰጠ።
71ከአባቶች፡ቤቶች፡አለቃዎችም፡ዐያሌዎቹ፡በሥራው፡ቤተ፡መዛግብት፡ውስጥ፡ኻያ፡ሺሕ፡የወርቅ፡ ዳሪክ፥ኹለት፡ሺሕ፡ኹለት፡መቶም፡ምናን፡ብር፡ሰጡ።
72የቀሩትም፡ሕዝብ፡የሰጡት፡ኻያ፡ሺሕ፡የወርቅ፡ዳሪክና፡ኹለት፡ሺሕ፡ምናን፡ብር፥ስድሳ፡ሰባትም፡ የካህናት፡ልብስ፡ነበረ።
73ካህናቱና፡ሌዋውያኑም፥በረኛዎቹና፡መዘምራኑም፡ከሕዝቡም፡ዐያሌዎቹ፥ናታኒምም፥እስራኤልም፡ዅሉ፡ በከተማዎቻቸው፡ተቀመጡ።