Skip to content
← Nehemiah

Chapter 6 · Amharic

Nehemiah

1እንዲህም፡ኾነ፤ቅጥሩን፡እንደ፡ሠራኹ፥ከፍራሹም፡አንዳች፡እንዳልቀረበት፡ሰንባላጥና፡ጦብያ፡ ዐረባዊውም፡ጌሳም፡የቀሩትም፡ጠላቶቻችን፡ሰሙ፤ነገር፡ግን፥እስከዚያ፡ጊዜ፡ድረስ፡በበሮቹ፡ውስጥ፡ ሳንቃዎቹን፡አላቆምኹም፡ነበር።

2ሰንባላጥና፡ጌሳም፦መጥተኽ፡በኦኖ፡ቈላ፡ውስጥ፡ባሉት፡መንደሮች፡እንገናኝ፡ብለው፡ላኩብኝ፤ነገር፡ ግን፥ክፉ፡ያደርጉብኝ፡ዘንድ፡ያስቡ፡ነበር።

3እኔም፦ትልቅ፡ሥራ፡እሠራለኹ፥እወርድም፡ዘንድ፡አይቻለኝም፤ሥራውን፡ትቼ፡ወደ፡እናንተ፡ በመውረዴ፡ስለ፡ምን፡ሥራው፡ይታጐላል፧ብዬ፡መልእክተኛዎችን፡ላክኹባቸው።

4እንዲህም፡ቃል፡አራት፡ጊዜ፡ላኩብኝ፤እኔም፡እንደ፡ፊተኛው፡ቃል፡መለስኹላቸው።

5ሰንባላጥም፡እንደ፡ፊተኛው፡ጊዜ፡ብላቴናውን፡ዐምስተኛ፡ጊዜ፡ላከብኝ፤

6በእጁም፡ውስጥ፦አንተና፡አይሁድ፡ዐመፅ፡እንድታስቡ፥ስለዚህም፡ቅጥሩን፡እንድትሠራ፥ንጉሣቸውም፡ ትኾን፡ዘንድ፡እንድትወድ፟፡በአሕዛብ፡ዘንድ፡ተሰምቷል።

7ደግሞም፦ንጉሥ፡በይሁዳ፡አለ፡ብለው፡ስለ፡አንተ፡በኢየሩሳሌም፡ይናገሩ፡ዘንድ፡ነቢያትን፡ አቁመኻል፤አኹንም፡ለንጉሡ፡ይህን፡ቃል፡ያወሩለታል፤እንግዲህ፡መጥተኽ፡በአንድነት፡እንማከር፡የሚል፡ ክፍት፡ደብዳቤ፡ነበረ።

8እኔም፦አንተ፡ከልብኽ፡ፈጥረኸዋል፡እንጂ፡እንደተናገርኸው፡ነገር፡ምንም፡የለም፡ብዬ፡ላክኹበት።

9እነርሱም፡ዅሉ፡ሥራው፡እንዳይፈጸም፦እጃቸው፡ይደክማል፡ብለው፡ያስፈራሩን፡ዘንድ፡ ወደዱ፤አኹንም፥አምላክ፡ሆይ፥እጄን፡አበርታ።

10እኔም፡ወደመሔጣብኤል፡ልጅ፡ወደድላያ፡ልጅ፡ወደሸማያ፡ቤት፡ገባኹ፤ርሱም፡ተዘግቶ፡ ነበርና፦በእግዚአብሔር፡ቤት፡በመቅደሱ፡ውስጥ፡እንገናኝ፡የመቅደሱንም፡ደጆች፡እንዝጋ፤እነርሱ፡መጥተው፡ ይገድሉኻልና፥በሌሊትም፡ይገድሉኽ፡ዘንድ፡ይመጣሉና፡አለ።

11እኔም፦እንደ፡እኔ፡ያለ፡ሰው፡የሸሸና፥ነፍሱንስ፡ያድን፡ዘንድ፡ወደ፡መቅደስ፡የገባ፡ማን፡ነው፧እኔስ፡ አልገባም፡አልኹት።

12እግዚአብሔርም፡ልኮት፡እንዳልነበረ፥በእኔ፡ላይ፡ግን፡ትንቢት፡እንደ፡ተናገረ፥እንሆ፥ዐወቅኹ፤ጦብያና፡ ሰንባላጥም፡ገዝተውት፡ነበር።

13ይህንም፡ነገር፡አደርግና፡እበድል፡ዘንድ፥በእኔም፡ላይ፡ክፋት፡እንዲናገሩና፡እንዲያላግጡ፡ያስፈራራኝ፡ ዘንድ፡ተገዝቶ፡ነበር።

14አምላኬ፡ሆይ፥ስለዚህ፡ሥራቸው፡ጦብያንና፡ሰንባላጥን፡ያስፈራሩኝም፡ዘንድ፡የወደዱትን፡ነቢዪቱን፡ ኖዓድያን፡የቀሩትንም፡ነቢያት፡ዐስብ።

15ቅጥሩም፡በኤሉል፡ወር፡በኻያ፡ዐምስተኛው፡ቀን፡በዐምሳ፡ኹለት፡ቀን፡ውስጥ፡ተጨረሰ።

16ጠላቶቻችንም፡ዅሉ፡ይህን፡በሰሙ፡ጊዜ፡በዙሪያችን፡የነበሩ፡አሕዛብ፡ዅሉ፡ፈሩ፥በራሳቸውም፡ዐሳብ፡ እጅግ፡ተዋረዱ፥ይህም፡ሥራ፡በእግዚአብሔር፡እንደ፡ተደረገ፡ዐወቁ።

18ጦብያም፡የኤራ፡ልጅ፡የሴኬንያ፡ዐማች፡ስለ፡ነበረ፥ልጁም፡ይሆሐናን፡የቤራክያን፡ልጅ፡ የሜሱላምን፡ሴት፡ልጅ፡ስላገባ፥በይሁዳ፡ብዙ፡ሰዎች፡ከርሱ፡ጋራ፡ተማምለው፡ነበርና፥በዚያ፡ወራት፡ብዙ፡ የይሁዳ፡አለቃዎች፡ወደ፡ጦብያ፡ደብዳቤዎች፡ይልኩ፡ነበር፥የጦብያም፡ደብዳቤዎች፡ወደ፡እነርሱ፡ይመጡ፡ ነበር።

19ደግሞም፡በፊቴ፡ስለ፡ርሱ፡መልካም፡ይናገሩ፡ነበር፥ቃሌንም፡ያወሩለት፡ነበር፤ጦብያም፡ሊያስፈራራኝ፡ ደብዳቤዎችን፡ይልክ፡ነበር። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source