Skip to content
← Nehemiah

Chapter 5 · Amharic

Nehemiah

1በወንድሞቻቸውም፡በአይሁድ፡ላይ፡ትልቅ፡የሕዝቡና፡የሚስቶቻቸው፡ጩኸት፡ኾነ።

2ዐያሌዎቹም፦ወንዶችና፡ሴቶች፡ልጆቻችን፡ብዙዎች፡ናቸው፤በልተንም፡በሕይወት፡እንድንኖር፡እኽልን፡ እንሸምት፡ይሉ፡ነበር።

3ዐያሌዎቹም፦ከራብ፡የተነሣ፡እኽልን፡እንሸምት፡ዘንድ፡ዕርሻችንና፡ወይናችንን፡ቤታችንንም፡አስይዘናል፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ይሉ፡ነበር።

4ሌላዎቹም፦ለንጉሡ፡ግብር፡ዕርሻችንንና፡ወይናችንን፡አስይዘን፡ገንዘብ፡ተበድረናል፤

5አኹንም፡ሥጋችን፡እንደ፡ወንድሞቻችን፡ሥጋ፥ልጆቻችንም፡እንደ፡ልጆቻቸው፡ናቸው፤እንሆም፡ ወንዶችና፡ሴቶች፡ልጆቻችን፡ባሪያዎች፡ይኾኑ፡ዘንድ፡ሰጥተናል፥ከሴቶችም፡ልጆቻችን፡ባሪያዎች፡ኾነው፡ የሚኖሩ፡አሉ፤ታላላቆችም፡ዕርሻችንና፡ወይናችንን፡ይዘዋልና፥ልናድናቸው፡አንችልም፡ይሉ፡ነበር።

6እኔም፡ጩኸታቸውንና፡ይህን፡ቃል፡በሰማኹ፡ጊዜ፡እጅግ፡ተቈጣኹ።

7በልቤም፡ዐሰብኹ፥ታላላቆቹንና፡ሹማምቱንም፦ዅላችኹ፡እያንዳንዳችኹ፡ወለድ፡ትወስዳላችኹ፡ብዬ፡ ተጣላዃቸው፤ትልቅም፡ጉባኤ፡ሰበሰብኹባቸው።

8እኔም፦ለአሕዛብ፡የተሸጡትን፡ወንድሞቻችንን፡አይሁድን፡በፈቃዳችን፡ተቤዠን፤እናንተስ፡ ወንድሞቻችኹን፡ትሸጣላችኹን፧እነርሱስ፡ለእኛ፡የተሸጡ፡ይኾናሉን፧አልዃቸው።እነርሱም፡ዝም፡ አሉ፥መልስም፡አላገኙም።

9ደግሞም፡አልኹ፦የምታደርጉት፡ነገር፡መልካም፡አይደለም፤ጠላቶቻችን፡አሕዛብ፡እንዳይሰድቡን፡ አምላካችንን፡በመፍራት፡ትኼዱ፡ዘንድ፡አይገ፟ባ፟ችኹምን፧

10እኔም፡ደግሞ፡ወንድሞቼም፡ብላቴናዎቼም፡ገንዘብና፡እኽል፡ለእነርሱ፡አበድረናል፤እባካችኹ፥ይህን፡ ወለድ፡እንተውላቸው።

11ዕርሻቸውንና፡ወይናቸውን፡ወይራቸውንና፡ቤታቸውንም፡ከነርሱም፡የወሰዳችኹትን፡ገንዘቡንና፡ እኽሉን፥ወይን፡ጠጁንና፡ዘይቱን፡ከመቶ፡እጅ፡አንድ፡እጅ፡እባካችኹ፡ዛሬ፡መልሱላቸው።

12እነርሱም፦እንመልስላቸዋለን፥ከነርሱም፡ምንም፡አንሻም፤እንደ፡ተናገርኽ፡እንዲሁ፡እናደርጋለን፡ አሉ።ካህናቱንም፡ጠርቼ፡እንደዚህ፡ነገር፡ያደርጉ፡ዘንድ፡አማልዃቸው።

13ደግሞም፡ልብሴን፡አራገፍኹና፦ይህን፡ነገር፡የማያደርገውን፡ሰው፡ከቤቱና፡ከሥራው፡እንዲሁ፡ እግዚአብሔር፡ያራግፈው፤እንዲሁም፡የተራገፈና፡ባዶ፡ይኹን፡አልኹ።ጉባኤውም፡ዅሉ፦አሜን፡ አሉ፥እግዚአብሔርንም፡አመሰገኑ፤ሕዝቡም፡እንደዚህ፡ነገር፡አደረጉ።

14ንጉሡም፡በይሁዳ፡ምድር፡ላይ፡አለቃ፡እኾን፡ዘንድ፡ካዘዘኝ፡ጊዜ፡ዠምሮ፡ከንጉሡ፡ከአርጤክስስ፡ ከኻያኛው፡ዓመት፡እስከ፡ሠላሳ፡ኹለተኛው፡ዓመት፡ድረስ፡ዐሥራ፡ኹለት፡ዓመት፡ያኽል፡እኔና፡ወንድሞቼ፡ ለአለቃ፡የሚገ፟ባ፟ውን፡ሥንቅ፡አልበላንም።

15ከእኔ፡አስቀድመው፡የነበሩት፡አለቃዎች፡ግን፡በሕዝቡ፡ላይ፡አክብደው፡ነበር፤ስለ፡እንጀራውና፡ስለ፡ ወይኑ፡አርባ፡ሰቅል፡ብር፡ይወስዱ፡ነበር፤ሎሌዎቻቸውም፡ደግሞ፡በሕዝቡ፡ላይ፡ይሠለጥኑ፡ነበር፤እኔ፡ግን፡ እግዚአብሔርን፡ስለ፡ፈራኹ፡እንዲህ፡አላደረግኹም።

16ደግሞም፡አጥብቄ፡የቅጥሩን፡ሥራ፡ሠራኹ፥ዕርሻም፡አልገዛንም፤ብላቴናዎቼም፡ዅሉ፡ወደዚያው፡ወደ፡ ሥራው፡ተሰበሰቡ።

17ደግሞም፡በዙሪያችን፡ካሉት፡አሕዛብ፡ወደ፡እኛ፡ከመጡት፡ሌላ፡ከአይሁድና፡ከሹማምቱ፡መቶ፡ዐምሳ፡ ሰዎች፡በገበታዬ፡ነበሩ።

18ከወፎችም፡በቀር፡ላንድ፡ቀን፡አንድ፡በሬና፡ስድስት፡የሰቡ፡በጎች፥በዐሥር፡በዐሥር፡ቀንም፡ብዙ፡ልዩ፡ ልዩ፡ዐይነት፡ወይን፡ጠጅ፡ይዘጋጅልኝ፡ነበር፤ነገር፡ግን፥አገዛዝ፡በሕዝቡ፡ላይ፡ከብዶ፡ነበርና፥ለአለቃ፡ የሚገ፟ባ፟ውን፡ሥንቅ፡አልሻም፡ነበር።

19አምላኬ፡ሆይ፥ለዚህ፡ሕዝብ፡ያደረግኹትን፡ዅሉ፡ለበጎነት፡ዐስብልኝ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source