Skip to content
← Nehemiah

Chapter 4 · Amharic

Nehemiah

1ሰንባላጥም፡ቅጥሩን፡እንደ፡ሠራን፡በሰማ፡ጊዜ፡እጅግ፡ተቈጣ፥ተበሳጨም፥በአይሁድም፡አላገጠ።

2በወንድሞቹና፡በሰማርያ፡ሰራዊትም፡ፊት፦እነዚህ፡ደካማዎች፡አይሁድ፡የሚሠሩት፡ምንድር፡ ነው፧ይተዉላቸዋልን፧ይሠዋሉን፧ባንድ፡ቀንስ፡ይጨርሳሉን፧የተቃጠለውንስ፡ድንጋይ፡ከፍርስራሹ፡መልሰው፡ ያድኑታልን፧ብሎ፡ተናገረ።

3አሞናዊውም፡ጦብያ፡በአጠገቡ፡ቆሞ፦በድንጋይ፡በሚሠሩት፡ቅጥራቸው፡ላይ፡ቀበሮ፡ቢመጣበት፡ ያፈርሰዋል፡አለ።

4አምላካችን፡ሆይ፥ተንቀናልና፥ስማ፤ስድባቸውን፡በራሳቸው፡ላይ፡መልስባቸው፤በምርኮ፡አገር፡ለብዝበዛ፡ አሳልፈኽ፡ስጣቸው።

5በደላቸውንም፡አትክደን፥ኀጢአታቸውም፡ከፊትኽ፡አይደምሰስ፤በሠራተኛዎች፡ፊት፡አስቈጥተውኻልና።

6ቅጥሩንም፡ሠራን፤ቅጥሩም፡ዅሉ፡እስከ፡እኩሌታው፡ድረስ፡ተጋጠመ፤የሕዝቡም፡ልብ፡ለሥራው፡ ጨከነ።

7ሰንባላጥና፡ጦብያም፡ዐረባውያንም፡አሞናውያንም፡አሽዶዳውያንም፡የኢየሩሳሌም፡ቅጥር፡እየታደሰ፡እንደ፡ 244ዕብ.፥ሔናዳድ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ኼደ፥የፈረሰውም፡ሊጠገን፡እንደ፡ተዠመረ፡በሰሙ፡ጊዜ፡እጅግ፡ተቈጡ።

8መጥተውም፡ኢየሩሳሌምን፡ይወጉና፡ያሸብሩ፡ዘንድ፡ዅሉም፡በአንድነት፡ተማማሉ።

9ወደ፡አምላካችንም፡ጸለይን፥ከነርሱም፡የተነሣ፡በአንጻራቸው፡ተጠባባቂዎች፡በሌሊትና፡በቀን፡አደረግን።

10ይሁዳም፦የተሸካሚዎች፡ኀይል፡ደከመ፥ፍርስራሹም፡ብዙ፡ነው፤ቅጥሩንም፡እንሠራ፡ዘንድ፡አንችልም፡ አሉ።

11ጠላቶቻችንም፦ወደ፡መካከላቸው፡እስክንመጣና፡እስክንገድላቸው፡ድረስ፡ሥራቸውንም፡እስክናስተጓጕል፡ ድረስ፡አያውቁምና፡አያዩም፡አሉ።

12በአጠገባቸውም፡የተቀመጡት፡አይሁድ፡መጥተው፦ከስፍራው፡ዅሉ፡ይመጡብናል፡ብለው፡ዐሥር፡ጊዜ፡ ነገሩን።

13ከቅጥሩም፡በስተዃላ፡በኩል፡ባለው፡በታችኛው፡ስፍራ፡ሰይፋቸውን፡ጦራቸውንም፡ቀስታቸውንም፡አስይዤ፡ ሕዝቡን፡በየወገናቸው፡አቆምዃቸው።

14አይቼም፡ተነሣኹ፥ታላላቆቹንና፡ሹማምቱንም፡የቀሩትንም፡ሕዝብ፦አትፍሯቸው፤ታላቁንና፡የተፈራውን፡ ጌታ፡ዐስቡ፥ስለ፡ወንድሞቻችኹም፡ስለ፡ወንዶችና፡ስለ፡ሴቶች፡ልጆቻችኹም፡ስለ፡ሚስቶቻችኹም፡ስለ፡ ቤቶቻችኹም፡ተዋጉ፡አልዃቸው።

15ጠላቶቻችንም፡ይህ፡ነገር፡እንደ፡ደረሰልን፥እግዚአብሔርም፡ምክራቸውን፡ከንቱ፡እንዳደረገው፡ ሰሙ፤እኛም፡ዅላችን፡ወደ፡ቅጥሩ፡እያንዳንዳችን፡ወደ፡ሥራችን፡ተመለስን።

16ከዚያም፡ቀን፡ዠምሮ፡እኩሌቶቹ፡ብላቴናዎቼ፡ሥራ፡ይሠሩ፡ነበር፥እኩሌቶቹም፡ጋሻና፡ጦር፡ቀስትና፡ ጥሩርም፡ይዘው፡ነበር፤አለቃዎቹም፡ከይሁዳ፡ቤት፡ዅሉ፡በዃላ፡ይቆሙ፡ነበር።

17ቅጥሩንም፡የሚሠሩትና፡ተሸካሚዎቹ፡ባንድ፡እጃቸው፡ይሠሩ፡ነበር፥ባንድ፡እጃቸውም፡የጦር፡ መሣሪያቸውን፡ይይዙ፡ነበር።

18ዐናጢዎቹም፡ዅሉ፡እያንዳንዱ፡ሰይፉን፡በወገቡ፡ታጥቆ፡ይሠራ፡ነበር፤ቀንደ፡መለከትም፡የሚነፋ፡ በአጠገቤ፡ነበረ።

19ታላላቆቹንና፡ሹማምቱን፡የቀሩትንም፡ሕዝብ።ሥራው፡ታላቅና፡ሰፊ፡ነው፥እኛም፡በቅጥሩ፡ላይ፡ ተበታትነናል፥አንዱም፡ከኹለተኛው፡ርቋል፤

20የቀንደ፡መለከቱን፡ድምፅ፡ወደምትሰሙበት፡ስፍራ፡ወደዚያ፡ወደ፡እኛ፡ተሰብሰቡ፤አምላካችን፡ስለ፡ እኛ፡ይዋጋል፡አልዃቸው።

21ሥራውንም፡ሠራን፡ከማለዳ፡ወገግታም፡ዠምሮ፡ከዋክብት፡እስኪወጡ፡ድረስ፡እኩሌቶቹ፡ጦር፡ይይዙ፡ ነበር።

22ደግሞም፡በዚያ፡ጊዜ፡ሕዝቡን፦ዅላችኹ፡ከብላቴናዎቻችኹ፡ጋራ፡በኢየሩሳሌም፡ውስጥ፡ ዕደሩ፤በሌሊትም፡ጠባቂዎች፡ኹኑልን፥በቀንም፡ሥሩ፡አልዃቸው።

23እኔና፡ወንድሞቼም፡ብላቴናዎቼም፡በዃላዬም፡የነበሩት፡ጠባቂዎች፡ልብሳችንን፡አናወልቅም፡ነበር።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source