1ታላቁም፡ካህን፡ኤልያሴብ፡ወንድሞቹም፡ካህናት፡ተነሥተው፡የበግ፡በር፡ሠሩ፤ቀደሱትም፥ሳንቃዎቹንም፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org አቆሙ፤እስከሃሜአ ፡ግንብና፡እስከሐናንኤል፡ግንብ፡ድረስ፡ቀደሱት።
2በአጠገቡ፡የኢያሪኮ፡ሰዎች፡ሠሩ፤በአጠገባቸውም፡የአምሪ፡ልጅ፡ዘኩር፡ሠራ።
3የሃስናአ፡ልጆችም፡የዓሣ፡በር፡ሠሩ፤ሠረገላዎቹን፡አኖሩ፥ሳንቃዎቹንም፡አቆሙ፥ቍልፎቹንና፡ መወርወሪያዎቹንም፡አደረጉ።
4በአጠገባቸውም፡የአቆስ፡ልጅ፡የኦርዮ፡ልጅ፡ሜሪሞት፡ዐደሰ።በአጠገባቸውም፡የሜሴዜቤል፡ልጅ፡ የበራክያ፡ልጅ፡ሜሱላም፡ዐደሰ።በአጠገባቸውም፡የበዓና፡ልጅ፡ሳዶቅ፡ዐደሰ።
5በአጠገባቸውም፡ቴቁሐውያን፡ዐደሱ፤ታላላቆቻቸው፡ግን፡ለጌታቸው፡ሥራ፡ዐንገታቸውን፡አላዋረዱም።
6የፋሴሐ፡ልጅ፡ዮዳዔና፡የበሶድያ፡ልጅ፡ሜሱላም፡አሮጌውን፡በር፡ዐደሱ፤ሠረገላዎቹን፡ አኖሩ፥ሳንቃዎቹንም፡አቆሙ፥ቍልፎቹንና፡መወርወሪያዎቹንም፡አደረጉ።
7በአጠገባቸውም፡ገባዖናዊው፡መልጥያና፡ሜሮኖታዊው፡ያዶን፥የወንዙም፡ማዶ፡አለቃ፡ግዛት፡የኾኑ፡ የገባዖንና፡የምጽጳ፡ሰዎች፡ዐደሱ።
8በአጠገባቸውም፡ወርቅ፡አንጥረኛው፡የሐርሃያ፡ልጅ፡ዑዝኤል፡ዐደሰ።በአጠገቡም፡ከሽቱ፡ቀማሚዎች፡ የነበረ፡ሐናንያ፡ዐደሰ፤እስከ፡ሰፊው፡ቅጥር፡ድረስ፡ኢየሩሳሌምን፡ጠገኑ።
9በአጠገባቸውም፡የኢየሩሳሌም፡ግዛት፡እኩሌታ፡አለቃ፡የሆር፡ልጅ፡ረፋያ፡ዐደሰ።
10በአጠገባቸውም፡የኤርማፍ ሐጡስ ፡ልጅ፡ይዳያ፡በቤቱ፡አንጻር፡ያለውን፡ዐደሰ።በአጠገቡም፡የአሰበንያ ፡ልጅ፡ ፡ዐደሰ።
11የካሪም፡ልጅ፡መልክያ፥የፈሐት፡ሞዐብ፡ልጅም፡ዐሱብ፡ሌላውን፡ክፍልና፡የእቶኑን፡ግንብ፡ዐደሱ።
12በአጠገባቸውም፡የኢየሩሳሌም፡ግዛት፡እኩሌታና፡የመንደሮቿ፡አለቃ፡የአሎኤስ ፡ልጅ፡ሰሎም፡ዐደሰ።
13ሐኖንና፡የዛኖዋ፡ሰዎችም፡የሸለቆውን፡በር፡ዐደሱ፤ሠሩት፥ሳንቃዎቹንም፡አቆሙ፥ቍልፎቹንና፡ መወርወሪያዎቹንም፡አደረጉ፤ደግሞም፡እስከጕድፍ፡መጣያው፡በር፡ድረስ፡አንድ፡ሺሕ፡ክንድ፡የሚኾን፡ ቅጥር፡ሠሩ።
14የቤትሐካሪምም፡ግዛት፡አለቃ፡የሬካብ፡ልጅ፡መልክያ፡የጕድፍ፡መጣያውን፡በር፡ ዐደሰ፤ሠራው፥ሳንቃዎቹንም፡አቆመ፥ቍልፎቹንና፡መወርወሪያዎቹንም፡አደረገ።
15የምጽጳም፡ግዛት፡አለቃ፡የኮልሖዜ፡ልጅ፡ሰሎም፡የምንጩን፡በር፡ ዐደሰ፤ሠራው፥ከደነውም፥ሳንቃዎቹንም፡አቆመ፥ቍልፎቹንና፡መወርወሪያዎቹንም፡አደረገ፤ከዳዊትም፡ከተማ፡ እስከሚወርደው፡ደረጃ፡ድረስ፡በንጉሡ፡አትክልት፡አጠገብ፡ያለውን፡የሼላን፡መዋኛ፡ቅጥር፡ሠራ።
16ከርሱም፡በዃላ፡የቤትጹር፡ግዛት፡እኩሌታ፡አለቃ፡የዓዝቡቅ፡ልጅ፡ነሐምያ፡በዳዊት፡መቃብር፡አንጻር፡ እስካለው፡ስፍራ፥እስከተሠራውም፡መዋኛ፥እስከኀያላኑም፡ቤት፡ድረስ፡ዐደሰ።
17ከርሱም፡በዃላ፡ሌዋውያንና፡የባኒ፡ልጅ፡ሬሁም፡ዐደሱ።በአጠገባቸውም፡የቅዒላ፡ግዛት፡እኩሌታ፡አለቃ፡ ሐሸብያ፡ስለ፡ግዛቱ፡ዐደሰ።
18ከርሱም፡በዃላ፡የቅዒላ፡ግዛት፡እኩሌታ፡አለቃ፡የኤንሐዳድ፡ልጅ፡በዋይ፡ወንድሞቹም፡ዐደሱ።
19በአጠገቡም፡የምጽጳ፡አለቃ፡የኢያሱ፡ልጅ፡ኤጽር፡በማእዘኑ፡አጠገብ፡በጦር፡መሣሪያ፡ቤት፡አንጻር፡ ሌላውን፡ክፍል፡ዐደሰ።
20ከርሱም፡በዃላ፡የዘባይ፡ልጅ፡ባሮክ፡ከማእዘኑ፡ዠምሮ፡እስከታላቁ፡ካህን፡እስከኤልያሴብ፡ቤት፡ 239 ዕብ.፥ሜአህ፡(ምእት•መቶ)። 240ዕብ.፥ሐሩማፍ። 241 ዕብ.፥ሐሻብንያሕ። 242ዕብ.፥ሐጡ፟ሽ። 243ዕብ.፥ሀ፡ሎኄሽ፡(ለኋሲ•በለኈሳስ፡የሚናገረው)። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org መግቢያ፡ድረስ፡ሌላውን፡ክፍል፡ተግቶ፡ዐደሰ።
21ከርሱም፡በዃላ፡የአቆስ፡ልጅ፡የኦርዮ፡ልጅ፡ሜሪሞት፡ከኤልያሴብ፡ቤት፡መግቢያ፡ዠምሮ፡ እስከኤልያሴብ፡ቤት፡መጨረሻ፡ድረስ፡ሌላውን፡ክፍል፡ዐደሰ።
22ከርሱም፡በዃላ፡የቈላው፡ሰዎች፡ካህናቱ፡ዐደሱ።
23ከነርሱም፡በዃላ፡ብንያምና፡ዐሱብ፡በቤታቸው፡አንጻር፡ያለውን፡ዐደሱ።ከነርሱም፡በዃላ፡የሐናንያ፡ልጅ፡ የመዕሴያ፡ልጅ፡ዐዛርያስ፡በቤቱ፡አጠገብ፡ያለውን፡ዐደሰ።
24ከርሱም፡በዃላ፡የኤንሐደድ ፡ልጅ፡ቢንዊ፡ከዐዛርያስ፡ቤት፡ዠምሮ፡እስከ፡ማእዘኑ፡ድረስ፡ሌላውን፡ ክፍል፡ዐደሰ።
25የኡዛይ፡ልጅ፡ፋላል፡በማእዘኑ፡አንጻር፡ያለውንና፡በዘበኛዎች፡አደባባይ፡አጠገብ፡ከላይኛው፡የንጉሡ፡ ቤት፡ወጥቶ፡የቆመውን፡ግንብ፡ሠራ።ከርሱም፡በዃላ፡የፋሮስ፡ልጅ፡ፈዳያ፡ሠራ።
26ናታኒምም፡በዖፌል፡በውሃው፡በር፡አንጻር፡በምሥራቅ፡በኩል፡ወጥቶ፡በቆመው፡ግንብ፡አጠገብ፡ እስካለው፡ስፍራ፡ድረስ፡ተቀመጡ።
27ከርሱም፡በዃላ፡ቴቁሐውያን፡ወጥቶ፡በቆመው፡በታላቁ፡ግንብ፡አንጻር፡ያለውን፡እስከዖፌል፡ቅጥር፡ ድረስ፡ሌላውን፡ክፍል፡ዐደሱ።
28ከፈረሱ፡በር፡በላይ፡ካህናቱ፡እያንዳንዳቸው፡በየቤታቸው፡አንጻር፡ዐደሱ።
29ከዚያ፡በዃላ፡የኢሜር፡ልጅ፡ሳዶቅ፡በቤቱ፡አንጻር፡ዐደሰ።ከርሱም፡በዃላ፡የምሥራቁን፡በር፡ጠባቂ፡ የሴኬንያ፡ልጅ፡ሸማያ፡ዐደሰ።
30ከርሱ፡በዃላ፡የሰሌምያ፡ልጅ፡ሐናንያና፡የሴሌፍ፡ስድስተኛው፡ልጁ፡ሐኖን፡ሌላውን፡ክፍል፡ ዐደሱ።ከዚያም፡በዃላ፡የበራክያ፡ልጅ፡ሜሱላም፡በጓዳው፡አንጻር፡ያለውን፡ዐደሰ።
31ከርሱም፡በዃላ፡ከወርቅ፡አንጥረኛዎቹ፡የነበረ፡መልክያ፡እስከ፡ናታኒምና፡እስከነጋዴዎቹ፡ቤት፡ድረስ፡ በሐሚፍቃድ፡በር፡አንጻር፡ያለውን፡እስከማእዘኑ፡መውጫ፡ድረስ፡ዐደሰ።
32ከማእዘኑም፡መውጫ፡ዠምረው፡እስከበጉ፡በር፡ድረስ፡ወርቅ፡አንጥረኛዎችና፡ነጋዴዎች፡ዐደሱ።