Skip to content
← Nehemiah

Chapter 11 · Amharic

Nehemiah

1የሕዝቡም፡አለቃዎች፡በኢየሩሳሌም፡ተቀመጡ፤ከቀሩትም፡ሕዝብ፡ከዐሥሩ፡ክፍል፡አንዱ፡በቅድስቲቱ፡ ከተማ፡በኢየሩሳሌም፥ዘጠኙም፡በሌላዎች፡ከተማዎች፡ይቀመጡ፡ዘንድ፡ዕጣ፡ተጣጣሉ።

2ሕዝቡም፡በፈቃዳቸው፡በኢየሩሳሌም፡ለመቀመጥ፡የወደዱትን፡ሰዎች፡ዅሉ፡ባረኩ።

3በኢየሩሳሌምም፡የተቀመጡት፡የአገሩ፡አለቃዎች፡እነዚህ፡ናቸው፤እስራኤል፡ግን፡ካህናቱም፡ሌዋውያኑም፡ ናታኒምም፡የሰሎሞንም፡ባሪያዎች፡ልጆች፡እያንዳንዳቸው፡በየርስታቸውና፡በየከተማቸው፡በይሁዳ፡ከተማዎች፡ ተቀመጡ።

4ከይሁዳና፡ከብንያምም፡ልጆች፡እነዚህ፡በኢየሩሳሌም፡ተቀመጡ።ከይሁዳ፡ልጆች፤ከፋሬስ፡ልጆች፡ የመላልኤል፡ልጅ፡የሰፋጥያስ፡ልጅ፡የአማርያ፡ልጅ፡የዘካርያስ፡ልጅ፡የዖዝያ፡ልጅ፡ዐታያ ፤

5የሴሎናዊውም፡ልጅ፡የዘካርያስ፡ልጅ፡የዮያሪብ፡ልጅ፡የዓዳያ፡ልጅ፡የዖዛያ፡ልጅ፡የኮልሖዜ፡ልጅ፡ የባሮክ፡ልጅ፡መዕሴያ።

6በኢየሩሳሌም፡የተቀመጡት፡የፋሬስ፡ልጆች፡ዅሉ፡አራት፡መቶ፡ስድሳ፡ስምንት፡ጽኑዓን፡ነበሩ።

7የብንያምም፡ልጆች፡እነዚህ፡ናቸው፤የየሻያ፡ልጅ፡የኢቲኤል፡ልጅ፡የመዕሴያ፡ልጅ፡የቆላያ፡ልጅ፡ የፈዳያ፡ልጅ፡የዮእድ፡ልጅ፡የሜሱላም፡ልጅ፡ሰሉ።

8ከርሱም፡በዃላ፡ጌቤና፡ሳላይ፡ዘጠኝ፡መቶም፡ኻያ፡ስምንት።

9አለቃቸውም፡የዝክሪ፡ልጅ፡ኢዮኤል፡ነበረ፤የሐስኑአም፡ልጅ፡ይሁዳ፡በከተማው፡ላይ፡ኹለተኛ፡ነበረ።

10ከካህናቱ፤የዮያሪብ፡ልጅ፡ዮዳዔ፥ያኪን፥

11የእግዚአብሔርም፡ቤት፡አለቃ፡የአኪጦብ፡ልጅ፡የመራዮት፡ልጅ፡የሳዶቅ፡ልጅ፡የሜሱላም፡ልጅ፡ 245ዕብ.፥ዐታያህ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org የኪልቅያስ፡ልጅ፡ሰራያ፥

12የቤቱንም፡ሥራ፡የሠሩ፡ወንድሞቻቸው፡ስምንት፡መቶ፡ኻያ፡ኹለት፤የመልክያ፡ልጅ፡የፋስኮር፡ልጅ፡ የዘካርያስ፡ልጅ፡የአማሲ፡ልጅ፡የፈላልያ፡ልጅ፡የይሮሐም፡ልጅ፡ዓዳያ፥

13ወንድሞቹም፡የአባቶቹ፡ቤቶች፡አለቃዎች፡ኹለት፡መቶ፡አርባ፡ኹለት፤የኢሜር፡ልጅ፡የምሺሌሞት፡ ልጅ፡የአሕዛይ፡ልጅ፡የዔዝርኤል፡ልጅ፡ዐማስያ፥

14ወንድሞቻቸውም፡መቶ፡ኻያ፡ስምንት፡ጽኑዓን፡ኀያላን፤አለቃቸውም፡የሐግዶሊም፡ልጅ፡ዘብድኤል፡ ነበረ።

15ከሌዋውያንም፤የቡኒ፡ልጅ፡የዐሳብያ፡ልጅ፡የዐዝሪቃም፡ልጅ፡የዐሱብ፡ልጅ፡ሻማያ፤

16ከእግዚአብሔርም፡ቤት፡በሜዳ፡በነበረው፡ሥራ፡ላይ፡የነበሩ፡የሌዋውያን፡አለቃዎች፡ሳባታይና፡ዮዛባት፤

17በጸሎትም፡ጊዜ፡ምስጋናን፡የሚቀነቅኑ፡አለቃው፡የአሣፍ፡ልጅ፡የዘብዲ፡ልጅ፡የሚካ፡ልጅ፡ መታንያ፥በወንድሞቹም፡መካከል፡ኹለተኛ፡የነበረ፡በቅበቃር፥የኤዶታምም፡ልጅ፡የጋላል፡ልጅ፡የሳሙስ፡ ልጅ፡ዐብድያ።

18በቅድስቲቱ፡ከተማ፡የነበሩ፡ሌዋውያን፡ዅሉ፡ኹለት፡መቶ፡ሰማንያ፡አራት፡ነበሩ።

19በሮቹንም፡የሚጠብቁ፡በረኛዎቹ፥ዐቁብና፡ጤልሞን፡ወንድሞቻቸውም፥መቶ፡ሰባ፡ኹለት፡ነበሩ።

20ከእስራኤልም፡የቀሩት፡ከካህናትና፡ከሌዋውያንም፡እያንዳንዳቸው፡በየርስታቸው፡በይሁዳ፡ከተማዎች፡ዅሉ፡ ውስጥ፡ነበሩ።

21ናታኒምም፡በዖፌል፡ተቀምጠው፡ነበር፤ሲሐና፡ጊሽጳ፡በናታኒም፡ላይ፡ነበሩ።

22በእግዚአብሔርም፡ቤት፡ሥራ፡ላይ፡ከነበሩ፡መዘምራን፡ከአሣፍ፡ልጆች፡ወገን፡የሚካ፡ልጅ፡የመታንያ፡ ልጅ፡የሐሸብያ፡ልጅ፡የባኒ፡ልጅ፡ዖዚ፡በኢየሩሳሌም፡የሌዋውያን፡አለቃ፡ነበረ።

23ስለ፡እነርሱም፡የንጉሥ፡ትእዛዝ፡ነበረ፤የመዘምራኑም፡ሥርዐት፡ለየዕለቱ፡የተሠራ፡ነበረ።

24ከይሁዳም፡ልጅ፡ከዛራ፡ወገን፡የሜሴዜቤል፡ልጅ፡ፈታያ፥ስለሕዝቡ፡ነገር፡ዅሉ፡በንጉሡ፡አጠገብ፡ ነበረ።

25ስለ፡መንደሮቹና፡ስለ፡ርሾቻቸው፤ከይሁዳ፡ልጆች፡ዐያሌዎች፡በቂርያትአርባቅና፡በመንደሮቿ፥በዲቦንና፡ በመንደሮቿም፥በይቀብጽኤልና፡በመንደሮቿም፥

27በኢያሱ፥በሞላዳ፥በቤትጳሌጥ፥በሐጸርሹዓል፥

28በቤርሳቤሕና፡በመንደሮቿ፥በጺቅላግ፥

29በምኮናና፡በመንደሮቿ፥በዐይንሪሞን፥

30በጾርዓ፥በየርሙት፥በዛኖዋ፡በዓዶላም፡በመንደሮቻቸውም፥በለኪሶና፡በዕርሻዎቿ፥በዓዜቃና፡በመንደሮቿ፡ ተቀመጡ።እንዲሁ፡ከቤርሳቤሕ፡ዠምሮ፡እስከሄኖም፡ሸለቆ፡ድረስ፡ሰፈሩ።

31የብንያምም፡ልጆች፡ከጌባ፡ዠምሮ፡በማክማስ፥በጋያ፥

32በቤቴልና፡በመንደሮቿ፥በዐናቶት፥በኖብ፥

34በሐናንያ፥በሐጾር፥በራማ፥በጊቴም፥በሐዲድ፥

35በስቦይም፥በንበላት፥በሎድ፥በኦኖ፥በጌሐራሺም፡ተቀመጡ።

36በይሁዳም፡ከነበሩ፡ሌዋውያን፡ዐያሌ፡ክፍሎች፡ወደ፡ብንያም፡ኾኑ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source