1ከሰላትያል፡ልጅ፡ከዘሩባቤልና፡ከኢያሱ፡ጋራ፡የወጡት፡ካህናትና፡ሌዋውያን፡እነዚህ፡ነበሩ፤
2ሰራያ፥ኤርምያስ፥ዕዝራ፥አማርያ፥
3መሉክ፥ሐጡስ፥ሴኬንያ፥ሬሁም፥ሜሪሞት፥
5አዶ፥ጌንቶን፥አብያ፥ሚያሚን፡
6መዓድያ፥ቢልጋ፥ሸማያ፥ዮያሪብ፥ዮዳዔ፥
7ሰሉ ፥ዐሞቅ ፥ኬልቅያስ ፥ዮዳዔ፤እነዚህ፡በኢያሱ፡ዘመን፡የካህናቱና፡የወንድሞቻቸው፡አለቃዎች፡ ነበሩ።
8ሌዋውያኑም፤ኢያሱ፥ቢንዊ፥ቀድምኤል፥ሰራብያ፥ይሁዳ፥ከወንድሞቹም፡ጋራ፡በመዘምራን፡ላይ፡የነበረ፡ መታንያ።
9ወንድሞቻቸውም፡በቅቡቅያና፡ዑኒ፡በየሰሞናቸው፡በአንጻራቸው፡ነበሩ።
10ኢያሱም፡ዮአቂም ን፡ወለደ፥ዮአቂምም፡ኤልያሴብን፡ወለደ፥ኤልያሴብም፡ዮአዳን፡ወለደ፥
11ዮአዳም፡ዮናታንን፡ወለደ፥ዮናታንም፡ያዱአን፡ወለደ።
12በዮአቂምም፡ዘመን፡የአባቶች፡ቤቶች፡አለቃዎች፡እነዚህ፡ካህናቱ፡ነበሩ፤ከሰራያ፡ምራያ፥
13ከኤርምያስ፡ሐናንያ፥ከዕዝራ፡ሜሱላም፥
14ከአማርያ፡ይሆሐናን፥ከመሉኪ፡ዮናታን፥
15ከሰበንያ፡ዮሴፍ፥ከካሪም፡ዓድና፥ከመራዮት፡ሔልቃይ፥
16ከአዶ፡ዘካርያስ፥ከጌንቶን፡ሜሱላም፥
17ከአብያ፡ዚክሪ፥ከሚያሚን ፡ሞዐድያ፥
18ፈልጣይ፥ከቢልጋ፡ሳሙስ፥ከሸማያ፡ዮናታን፥
19ከዮያሪብ፡መትናይ፥ከዮዳዔ፡ዖዚ፥
20ከሳላይ፡ቃላይ፥ከዐሞቅ፡ዔቤር፥
21ከኬልቅያስ፡ሐሸብያ፥ከዮዳዔ፡ናትናኤል።
22ከሌዋውያኑም፡በኤልያሴብና፡በዮአዳ፥በዮሐናንና፡በያዱአ፡ዘመን፡የአባቶች፡ቤቶች፡አለቃዎች፡ ተጻፉ፤ካህናቱም፡በፋርሳዊው፡በዳርዮስ፡መንግሥት፡ዘመን፡ተጻፉ።
23የሌዊ፡ልጆች፡የአባቶች፡ቤቶች፡አለቃዎች፡እስከኤልያሴብ፡ልጅ፡እስከዮሐናን፡ዘመን፡ድረስ፡በታሪክ፡ መጽሐፍ፡ተጻፉ።
24የሌዋውያኑም፡አለቃዎች፤ሐሸብያ፥ሰራብያ፥የቀድምኤልም፡ልጅ፡ኢያሱ፡እንደእግዚአብሔር፡ሰው፡ እንደ፡ዳዊት፡ትእዛዝ፡በየሰሞናቸው፡በወንድሞቻቸው፡ፊት፡ለፊት፡ያከብሩና፡ያመሰግኑ፡ነበር።
25መታንያ፥በቅቡቅያ፥ዐብድዩ ፥ሜሱላም፥ጤልሞን፥ዐቁብ፡በበሮች፡አጠገብ፡የሚገኙትን፡ዕቃ፡ቤቶች፡ ለመጠበቅ፡በረኛዎች፡ነበሩ።
26እነዚህ፡በኢዮሴዴቅ፡ልጅ፡በኢያሱ፡ልጅ፡በዮአቂም፡በአለቃውም፡በነሐምያ፡በጸሓፊውም፡በካህኑ፡ 246ዕብ.፥ሰሉ፟፡(የተሰላ፥የተለካ)። 247ዕብ.፥ዐሞቅ፡(ዕመቅ•ጥልቀት፣ጕድጓድ)። 248ዕብ.፥ኂልቂያህ፡(የጌታ፡ክፍል)። 249ዕብ.፥ዮያቂም፡(ያቀውም፡እግዚእ•ጌታ፡ያቆማል)። 250 ዕብ.፥ሚንያሚን፡(እምየማን•ከቀኝ)። 251 ዕብ.፥ዖባድያህ፡(ዐብደ፡እግዚእ፥የጌታ፡አገልጋይ)። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org በዕዝራ፡ዘመን፡ነበሩ።
27የኢየሩሳሌምንም፡ቅጥር፡በቀደሱ፡ጊዜ፡ቅዳሴውን፡በደስታና፡በምስጋና፡በመዝሙርም፡በጸናጽልም፡ በበገናም፡በመሰንቆም፡ለማድረግ፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡ያመጧቸው፡ዘንድ፡ሌዋውያኑን፡በየስፍራቸው፡ዅሉ፡ ፈለጉ።
29መዘምራኑም፡በኢየሩሳሌም፡ዙሪያ፡መንደሮች፡ሠርተው፡ነበርና፥የመዘምራኑ፡ልጆች፡ከኢየሩሳሌም፡ ዙሪያና፡ከነጦፋውያን፡መንደሮች፥ከቤትገልገላም፥ከጌባና፡ከዓዝሞት፡ዕርሻዎች፡ተሰበሰቡ።
30ካህናቱና፡ሌዋውያኑም፡ራሳቸውን፡አነጹ፤ሕዝቡንም፡በሮቹንም፡ቅጥሩንም፡አነጹ።
31የይሁዳንም፡አለቃዎች፡ወደ፡ቅጥሩ፡ላይ፡አወጣዃቸው፤አመስጋኞቹንም፡በኹለት፡ታላላቅ፡ተርታ፡ አቆምዃቸው፤አንዱም፡ወደ፡ቀኝ፡በቅጥሩ፡ላይ፡ወደጕድፍ፡መጣያው፡በር፡ኼደ።
32ከነርሱም፡በዃላ፡ሆሻያ፥የይሁዳም፡አለቃዎች፡እኩሌታ፥
33ዐዛርያስ፥ዕዝራ፥
34ሜሱላም፥ይሁዳ፥ብንያም፥ሸማያ፥ኤርምያስ፥
35መለከትም፡ይዘው፡ከካህናቱ፡ልጆች፡ዐያሌዎች፥የአሣፍም፡ልጅ፡የዘኩር፡ልጅ፡የሚካያ፡ልጅ፡ የመታንያ፡ልጅ፡የሸማያ፡ልጅ፡የዮናታን፡ልጅ፡ዘካርያስ፥
36ወንድሞቹም፡ሸማያ፥ዔዝርኤል፥ሚላላይ፥ጊላላይ፥መዓይ፥ናትናኤል፥ይሁዳ፥ዐናኒ፡የእግዚአብሔርን፡ ሰው፡የዳዊትን፡የዜማውን፡ዕቃ፡ይዘው፡ኼዱ፤ጸሓፊውም፡ዕዝራ፡በፊታቸው፡ነበረ።
37በምንጭም፡በር፡አቅንተው፡ኼዱ፤በዳዊትም፡ከተማ፡ደረጃ፥በቅጥሩም፡መውጫ፥ከዳዊትም፡ቤት፡ በላይ፡እስከውሃው፡በር፡ድረስ፡በምሥራቅ፡በኩል፡ኼዱ።
38ኹለተኛውም፡የአመስጋኞቹ፡ተርታ፡ወደ፡ግራ፡ኼደ፤እኔና፡የሕዝቡም፡እኩሌታ፡በስተዃላቸው፡ ነበርን፤በቅጥሩም፡ላይ፥በእቶኑ፡ግንብ፡በላይ፡እስከ፡ሰፊው፡ቅጥር፡ድረስ፥ከኤፍሬምም፡በር፡በላይ፥
39በአሮጌው፡በርና፡በዓሣ፡በር፡በሐናንኤልም፡ግንብ፥በሃሜአ፡ግንብ፡እስከበጎች፡በር፡ድረስ፡ ኼዱ፤በዘበኛዎችም፡በር፡አጠገብ፡ቆሙ።
40እንዲሁ፡ኹለቱ፡የአመስጋኞች፡ተርታዎች፡በእግዚአብሔር፡ቤት፡ቆሙ፤ከነርሱም፡ጋራ፡እኔና፡ የአለቃዎች፡እኩሌታ፥
41ካህናቱም፡ኤልያቄም፥መዕሴያ፥ሚንያሚን፥ሚካያ፥ኤልዮዔናይ፥
42ዘካርያስ፥ሐናንያ፡መለከት፡ ይዘው፥መዕሴያ፥ሸማያ፥አልዓዛር፥ዖዚ፥ይሆሐናን፥መልክያ፥ዔላም፥ኤጽር፡ቆምን።መዘምራኑም፡በታላቅ፡ ድምፅ፡ዘመሩ፥አለቃቸውም፡ይዝረሕያ፡ነበረ።
43እግዚአብሔርም፡በታላቅ፡ደስታ፡ደስ፡አሠኝቷቸዋልና፥በዚያ፡ቀን፡ትልቅ፡መሥዋዕት፡አቀረቡ፥ደስም፡ አላቸው፤ሴቶቹና፡ልጆቹም፡ደግሞ፡ደስ፡አላቸው፤የኢየሩሳሌምም፡ደስታ፡ከሩቅ፡ተሰማ።
44ይሁዳም፡በአገልጋዮቹ፡ካህናትና፡ሌዋውያን፡ደስ፡ስላላቸው፥የካህናቱንና፡የሌዋውያኑን፡ዕድል፡ፈንታ፡ እንደ፡ሕጉ፡ከከተማዎች፡ዕርሻዎች፡ያከማቹ፡ዘንድ፡ለእጅ፡ማንሣት፡ቍርባንና፡ለበኵራት፡ለዓሥራትም፡ በየዕቃ፡ቤቶቹ፡ላይ፡በዚያ፡ቀን፡ሰዎች፡ተሾሙ።
45እነርሱም፡መዘምራኑና፡በረኛዎቹም፡የአምላካቸውን፡ሥርዐት፡የመንጻታቸውንም፡ሥርዐት፡እንደ፡ዳዊትና፡ እንደ፡ልጁ፡እንደ፡ሰሎሞን፡ትእዛዝ፡ጠበቁ።
46አስቀድሞም፡በዳዊትና፡በአሣፍ፡ዘመን፡እግዚአብሔርን፡በዜማ፡ለማመስገንና፡ለማክበር፡የመዘምራን፡ አለቃዎች፡ነበሩ።
47እስራኤልም፡ዅሉ፡በዘሩባቤልና፡በነሐምያ፡ዘመን፡ለመዘምራኑና፡ለበረኛዎቹ፡ዕድል፡ፈንታቸውን፡በየዕለቱ፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ይሰጡ፡ነበር፤የተቀደሰውንም፡ነገር፡ለሌዋውያን፡ሰጡ፥ሌዋውያኑም፡ከተቀደሰው፡ነገር፡ለአሮን፡ልጆች፡ሰጡ።