1በዃለኛው፡ዝናብ፡ጊዜ፡ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ዝናቡን፡ለምኑ፤እግዚአብሔር፡መብረቅ፡ ያደርጋል፤ርሱም፡የበልግ፡ዝናብን፡ለያንዳንዱም፡በሜዳ፡ውስጥ፡ሣርን፡ይሰጣል።
2ተራፊም፡ከንቱነትን፡ተናግረዋልና፥ሟርተኛዎችም፡ውሸትን፡አይተዋልና፤ሕልምንም፡የሚያዩ፡በሐሰት፡ ተናግረዋል፥በከንቱም፡ያጽናናሉ፤እረኛም፡የላቸውምና፡እንደ፡በጎች፡ተቅበዝብዘዋል፡ተጨንቀውማል።
3ቍጣዬ፡በእረኛዎች፡ላይ፡ነዷ፟ል፥አውራ፡ፍየሎችንም፡እቀጣለኹ፤የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔርም፡ የይሁዳን፡ቤት፡መንጋውን፡ጐብኝቷል፥በሰልፍም፡ውስጥ፡እንዳለ፡እንደ፡ክብሩ፡ፈረስ፡ያደርጋቸዋል።
4ከርሱ፡ዘንድ፡የማእዘኑ፡ድንጋይ፥ከርሱም፡ዘንድ፡ችንካሩ፥ከርሱም፡ዘንድ፡የሰልፉ፡ቀስት፥ከርሱም፡ ዘንድ፡አስገባሪው፡ዅሉ፡ባንድ፡ላይ፡ይመጣሉ።
5በሰልፍም፡ጊዜ፡ጠላቶቻቸውን፡በመንገድ፡ጭቃ፡ውስጥ፡እንደሚረግጡ፡ኀያላን፡ይኾናሉ፤እግዚአብሔርም፡ ከነርሱ፡ጋራ፡ነውና፥ይዋጋሉ፥ፈረሰኛዎችም፡ያፍራሉ።
6ወድጃቸዋለኹና፡የይሁዳን፡ቤት፡አበረታለኹ፥የዮሴፍንም፡ቤት፡ አድናለኹ፤አደላድላቸዋለኹም፤እመልሳቸዋለኹ፤እኔም፡አምላካቸው፡እግዚአብሔር፡ነኝና፥እኔም፡ እሰማቸዋለኹና፡እንዳልጣልዃቸው፡ይኾናሉ።
7የኤፍሬምም፡ሰዎች፡እንደ፡ኀያላን፡ይኾናሉ፥ልባቸውም፡የወይን፡ጠጅ፡እንደ፡ጠጣ፡ሰው፡ደስ፡ ይለዋል፤ልጆቻቸውም፡አይተው፡ደስ፡ይላቸዋል፥ልባቸውም፡በእግዚአብሔር፡ሐሤት፡ያደርጋል።
8ተቤዥቻቸዋለኹና፡በፉጨት፡ጠርቼ፡እሰበስባቸዋለኹ፤ቀድሞም፡በዝተው፡እንደ፡ነበሩ፡ይበዛሉ።
9በአሕዛብም፡መካከል፡ብዘራቸው፡እንኳ፡በሩቅ፡አገር፡ሳሉ፡ያስቡኛል፥ከልጆቻቸውም፡ጋራ፡በሕይወት፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ይኖራሉ፥ይመለሱማል።
10ከግብጽም፡ምድር፡እመልሳቸዋለኹ፥ከአሶርም፡እሰበስባቸዋለኹ፤ወደ፡ገለዓድና፡ወደሊባኖስ፡ምድር፡ አመጣቸዋለኹ፥የሚበቃም፡ቦታ፡አይገኝላቸውም።
11ርሱም፡በጭንቅ፡ባሕር፡ያልፋል፥የባሕርንም፡ሞገድ፡ይመታል፥የወንዙም፡ጥልቅ፡ዅሉ፡ ይደርቃል፤የአሶርም፡ትዕቢት፡ይዋረዳል፥የግብጽም፡በትረ፡መንግሥት፡ይርቃል።
12በአምላካቸው፡በእግዚአብሔር፡አበረታቸዋለኹ፥በስሙም፡ይመካሉ፥ይላል፡እግዚአብሔር።