Skip to content
← Zechariah

Chapter 9 · Amharic

Zechariah

1የእግዚአብሔር፡ቃል፡ሸክም፡በሴድራክ፡ምድር፡ላይ፡ነው፥በደማስቆም፡ላይ፡ያርፋል፤የእግዚአብሔር፡ ዐይን፡ወደ፡ሰውና፡ወደእስራኤል፡ነገድ፡ዅሉ፡ዘንድ፡ነው፤

2ደግሞም፡በዳርቻዋ፡ባለችው፡በሐማት፡ላይ፥እጅግ፡ጠቢበኛዎች፡በኾኑ፡በጢሮስና፡በሲዶና፡ላይ፡ነው።

3ጢሮስም፡ምሽግን፡ለራሷ፡ሠርታለች፥ብሩንም፡እንደ፡ዐፈር፥ጥሩውንም፡ወርቅ፡እንደ፡መንገድ፡ጭቃ፡ አከማችታለች።

4እንሆ፥ጌታ፡ይገፋ፟ታል፥በባሕርም፡ላይ፡ያለውን፡ብርታቷን፡ይመታል፤ርሷም፡በእሳት፡ትበላለች።

5አስቀሎና፡አይታ፡ትፈራለች፤ጋዛ፡ደግሞ፡አይታ፡እጅግ፡ትታመማለች፤ዐቃሮንም፡እንዲሁ፥ተስፋዋ፡ ይቈረጣልና፤ንጉሡም፡ከጋዛ፡ይጠፋል፥በአስቀሎናም፡የሚቀመጥ፡አይገኝም።

6የተደባለቀ፡ወገን፡በአዛጦን፡ይቀመጣል፥የፍልስጥኤማውያንንም፡ትዕቢት፡አጠፋለኹ።

7ደሙንም፡ከአፉ፡ውስጥ፡ርኩሱንም፡ነገር፡ከጥርሱ፡መካከል፡አስወግዳለኹ፤ርሱም፡ደግሞ፡ለአምላካችን፡ ቅሬታ፡ይኾናል፤በይሁዳም፡እንደ፡አለቃ፡ይኾናል፥ዐቃሮንም፡እንደ፡ኢያቡሳዊ፡ይኾናል።

8እኔም፡ማንም፡እንዳይኼድና፡እንዳይመለስ፡እንደ፡ጠባቂ፡ጦር፡ኾኖ፡በቤቴ፡ዙሪያ፡ሰፈር፡ አደርጋለኹ፤አኹንም፡በዐይኔ፡አይቻለኹና፡ከዚህ፡በዃላ፡አስጨናቂ፡አያልፍባቸውም። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

9አንቺ፡የጽዮን፡ልጅ፡ሆይ፥እጅግ፡ደስ፡ይበልሽ፤አንቺ፡የኢየሩሳሌም፡ልጅ፡ሆይ፥እልል፡ በዪ፤እንሆ፥ንጉሥሽ፡ጻድቅና፡አዳኝ፡ነው፤ትሑትም፡ኾኖ፡በአህያም፥በአህያዪቱ፡ግልገል፡በውርንጫዪቱ፡ ላይ፡ተቀምጦ፡ወደ፡አንቺ፡ይመጣል።

10ሠረገላውንም፡ከኤፍሬም፡ፈረሱንም፡ከኢየሩሳሌም፡አጠፋለኹ፤የሰልፉም፡ቀስት፡ይሰበራል፥ለአሕዛብም፡ ሰላምን፡ይናገራል፤ግዛቱም፡ከባሕር፡እስከ፡ባሕር፥ከወንዙም፡እስከምድር፡ዳርቻ፡ድርስ፡ይኾናል።

11ላንቺም፡ደግሞ፡ስለ፡ቃል፡ኪዳንሽ፡ደም፥እስሮችሽን፡ውሃ፡ከሌለበት፡ጕድጓድ፡አውጥቻለኹ።

12እናንተ፡በተስፋ፡የምትኖሩ፡እስሮች፡ሆይ፥ወደ፡ጽኑ፡ዐምባ፡ተመለሱ፤ኹለት፡ዕጥፍ፡አድርጌ፡ እንድመልስልሽ፡ዛሬ፡እነግርሻለኹ።

13ይሁዳን፡ለእኔ፡ገትሬያለኹ፤ቀስቱን፡በኤፍሬም፡ሞልቻለኹ፤ጽዮን፡ሆይ፥ልጆችሽን፡በግሪክ፡ልጆች፡ ላይ፡አስነሣለኹ፥አንቺንም፡እንደ፡ኀያል፡ሰው፡ሰይፍ፡አደርግሻለኹ።

14እግዚአብሔርም፡በእነርሱ፡ላይ፡ይገለጣል፥ፍላጻውም፡እንደ፡መብረቅ፡ይወጣል፤ጌታ፡እግዚአብሔርም፡ መለከትን፡ይነፋል፥በደቡብም፡ዐውሎ፡ነፋስ፡ይኼዳል።

15የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡ይጠብቃቸዋል፤እነርሱም፡ይበሏቸዋል፥የወንጭፉንም፡ድንጋዮች፡ ይረግጣሉ፤እንደ፡ወይን፡ጠጅም፡ይጠጧቸዋል፥እንደ፡ጥዋዎችም፡እንደ፡መሠዊያም፡ማእዘኖች፡የተሞሉ፡ ይኾናሉ።

16በዚያም፡ቀን፡አምላካቸው፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ሕዝቡ፡መንጋ፡ያድናቸዋል፤እነርሱም፡ለአክሊል፡ እንደሚኾኑ፡እንደ፡ከበሩ፡ድንጋዮች፡ይኾናሉ፥በምድሩም፡ላይ፡ይብለጨለጫሉ።

17በጎነቱ፡እንዴት፡ታላቅ፡ነው! ውበቱስ፡እንዴት፡ታላቅ፡ነው! እኽል፡ጐበዛዝቱን፥ጕሽ፡ጠጅም፡ ቈነዣዥቱን፡ያለመልማል።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source