1ሊባኖስ፡ሆይ፥ደጆችኽን፡ክፈት፥እሳትም፡ዝግባዎችኽን፡ትብላ።
2የጥድ፡ዛፍ፡ሆይ፥ዝግባ፡ወድቋልና፥ከበርቴዎችም፡ጠፍተዋልና፥ዋይ፡በል፤እናንተም፡የባሳን፡ዛፎች፡ ሆይ፥ጽኑው፡ጫካ፡ተቈርጧልና፥ዋይ፡በሉ።
3የእረኛዎች፡ክብር፡ተዋርዷልና፥የዋይታቸው፡ድምፅ፡ተሰምቷል፤የዮርዳኖስ፡ትዕቢት፡ ተዋርዷልና፥የአንበሳዎች፡ግሣት፡ድምፅ፡ተሰምቷል።
4አምላኬ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ብሏል፦ለዕርድ፡የሚኾኑትን፡በጎች፡ጠብቅ።
5የገዟቸው፡ያርዷቸዋል፥ራሳቸውንም፡እንደ፡በደለኛዎች፡አድርገው፡አይቈጥሩም፤የሸጧቸውም፦ባለጠጋ፡ ኾነናልና፥እግዚአብሔር፡ይመስገን፡ይላሉ፤እረኛዎቻቸውም፡አይራሩላቸውም።
6ከእንግዲህ፡ወዲህ፡በምድር፡ላይ፡ለሚኖሩ፡አልራራም፥ይላል፡እግዚአብሔር፤እንሆም፥ሰውን፡ዅሉ፡ በባልንጀራውና፡በንጉሡ፡እጅ፡አሳልፌ፡እሰጣለኹ፤ምድሪቱንም፡ይመታሉ፥ከእጃቸውም፡አላድናቸውም።
7እኔም፡ለዕርድ፡የሚኾኑትን፡በጎች፥የመንጋውን፡ችግረኛዎች፡ጠበቅኹ።ኹለት፡በትሮችንም፡ ወሰድኹ፤የአንዲቱን፡ስም፡ውበት፡የኹለተኛዪቱንም፡ስም፡ማሰሪያ፡ብዬ፡ጠራኹ፤መንጋውንም፡ጠበቅኹ።
8ባንድ፡ወርም፡ሦስቱን፡እረኛዎች፡አጠፋኹ፤ነፍሴም፡ተሰቀቀቻቸው፥ነፍሳቸውም፡ደግሞ፡እኔን፡ጠላች።
9እኔም፦እናንተን፡አልጠብቅም፤የሚሞተው፡ይሙት፥የሚጠፋውም፡ይጥፋ፤የቀረውም፡እያንዳንዱ፡ የባልንጀራውን፡ሥጋ፡ይብላ፡አልኹ።
10እኔም፡ከሕዝቦች፡ዅሉ፡ጋራ፡የገባኹትን፡ቃል፡ኪዳኔን፡አፈርስ፡ዘንድ፡ውበት፡የተባለችውን፡በትሬን፡ ወስጄ፡ቈረጥኹ።
11በዚያም፡ቀን፡ተሰበረች፤እንዲሁም፡እኔን፡የተመለከቱ፡የመንጋው፡ችግረኛዎች፡የእግዚአብሔር፡ቃል፡ እንደ፡ነበረ፡ዐወቁ።
12እኔም፦ደስ፡ብሏችኹ፡እንደ፡ኾነ፡ዋጋዬን፡ስጡኝ፤ያለዚያ፡ግን፡ተዉት፡አልኹ።እነርሱም፡ለዋጋዬ፡ ሠላሳ፡ብር፡መዘኑ።
13እግዚአብሔርም፦የተስማሙበትን፡የከበረውን፡ዋጋዬን፡በግምጃ፡ቤቱ፡ውስጥ፡አኑረው፡አለኝ።እኔም፡ ሠላሳውን፡ብር፡ወስጄ፡በእግዚአብሔር፡ቤት፡ባለው፡በግምጃ፡ቤቱ፡ውስጥ፡አኖርኹት።
14በይሁዳና፡በእስራኤል፡መካከል፡ያለውንም፡ወንድማማችነት፡እሰብር፡ዘንድ፡ማሰሪያ፡የተባለችውን፡ ኹለተኛዪቱን፡በትሬን፡ቈረጥኹ።
15እግዚአብሔርም፡እንዲህ፡አለኝ፦ዳግመኛም፡የሰነፍን፡እረኛ፡ዕቃ፡ውሰድ።
16እንሆ፥በአገሩ፡ውስጥ፡እረኛ፡አስነሣለኹ፤ርሱም፡የጠፋውን፡አያስብም፥የባዘነውን፡ አይፈልግም፥የተሰበረውን፡አይጠግንም፤የዳነውንም፡አይቀልብም፥ነገር፡ግን፥የሰባውን፡ሥጋ፡ ይበላል፥ሰኰናውንም፡ይቀለጣጥማል። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
17መንጋውን፡ለሚተው፡ለምናምንቴ፡እረኛ፡ወዮለት! ሰይፍ፡በክንዱና፡በቀኝ፡ዐይኑ፡ላይ፡ይኾናል፤ክንዱም፡ አጥብቃ፡ትደርቃለች፥ቀኝ፡ዐይኑም፡ፈጽሞ፡ትጨልማለች።