1ስለ፡እስራኤል፡የተነገረ፡የእግዚአብሔር፡ቃል፡ሸክም፡ይህ፡ነው፦ሰማያትን፡የዘረጋ፥ምድርንም፡ የመሠረተ፥የሰውንም፡መንፈስ፡በውስጡ፡የሠራ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦
2እንሆ፥ኢየሩሳሌምን፡በዙሪያዋ፡ላሉት፡ለአሕዛብ፡ዅሉ፡የመንገድገድ፡ዋንጫ፡አደርጋታለኹ፤ደግሞም፡ ኢየሩሳሌም፡ስትከበብ፡በይሁዳ፡ላይ፡እንዲሁ፡ይኾናል።
3በዚያም፡ቀን፡ኢየሩሳሌምን፡ለአሕዛብ፡ዅሉ፡ከባድ፡ድንጋይ፡አደርጋታለኹ፤የሚሸከሟት፡ዅሉ፡እጅግ፡ ይቈስላሉ፤የምድርም፡አሕዛብ፡ዅሉ፡በላይዋ፡ላይ፡ይከማቻሉ።
4በዚያ፡ቀን፥ይላል፡እግዚአብሔር፥ፈረስን፡ዅሉ፡በድንጋጤ፥ተቀማጭንም፡በእብድነት፡ እመታለኹ፤ዐይኖቼንም፡በይሁዳ፡ላይ፡እከፍታለኹ፥የአሕዛብንም፡ፈረሶች፡ዅሉ፡በዕውርነት፡እመታለኹ።
5የይሁዳም፡አለቃዎች፡በልባቸው፦በኢየሩሳሌም፡ለሚኖሩ፡በአምላካቸው፡በሰራዊት፡ጌታ፡በእግዚአብሔር፡ ብርታት፡አለ፡ይላሉ።
6በዚያ፡ቀን፡የይሁዳን፡አለቃዎች፡በዕንጨት፡መካከል፡እንዳለ፡ትንታግ፥በነዶዎችም፡መካከል፡እንዳለ፡ እንደ፡ፋና፡ነበልባል፡አደርጋቸዋለኹ፤በቀኝና፡በግራ፡በዙሪያ፡ያሉትን፡አሕዛብ፡ዅሉ፡ይበላሉ፤ከዚያም፡ ወዲያ፡ኢየሩሳሌም፡በስፍራዋ፡በኢየሩሳሌም፡ትኖራለች።
7እግዚአብሔርም፡የዳዊት፡ቤት፡ክብርና፡የኢየሩሳሌም፡ሰዎች፡ክብር፡በይሁዳ፡ክብር፡ላይ፡እንዳይታበይ፡ የይሁዳን፡ድንኳኖች፡አስቀድሞ፡ያድናል።
8በዚያ፡ቀን፡እግዚአብሔር፡በኢየሩሳሌም፡ለሚኖሩት፡ይመክትላቸዋል፤በዚያም፡ቀን፡ከነርሱ፡መካከል፡ ደካማው፡እንደ፡ዳዊት፡ይኾናል፤የዳዊትም፡ቤት፡በፊታቸው፡እንደእግዚአብሔር፡መልአክ፡እንደ፡አምላክ፡ ይኾናል።
9በዚያም፡ቀን፡በኢየሩሳሌም፡ላይ፡የሚመጡትን፡አሕዛብ፡ዅሉ፡ለማጥፋት፡እጋደላለኹ።
10በዳዊትም፡ቤት፡ላይ፥በኢየሩሳሌምም፡በሚኖሩት፡ላይ፥የሞገስንና፡የልመናን፡መንፈስ፡አፈሳ፟ለኹ፤ወደ፡ ርሱም፡ወደወጉት፡ይመለከታሉ፤ሰውም፡ለአንድያ፡ልጁ፡እንደሚያለቅስ፡ያለቅሱለታል፥ሰውም፡ለበኵር፡ልጁ፡ እንደሚያዝን፡በመራራ፡ሐዘን፡ያዝኑለታል።
11በዚያ፡ቀን፡በመጊዶን፡ሜዳ፡እንደ፡ነበረው፡እንደ፡ሐዳድሪሞን፡ልቅሶ፡ታላቅ፡ልቅሶ፡በኢየሩሳሌም፡ ይኾናል።
12ምድሪቱም፡ታለቅሳለች፤እያንዳንዱ፡ወገን፡ለብቻው፥የዳዊት፡ቤት፡ወገን፡ለብቻው፥ሴቶቻቸውም፡ ለብቻቸው፤የናታን፡ቤት፡ወገን፡ለብቻው፥ሴቶቻቸውም፡ለብቻቸው፤
13የሌዊ፡ቤት፡ወገን፡ለብቻው፥ሴቶቻቸውም፡ለብቻቸው፤የሰሜኢ፡ወገን፡ለብቻው፥ሴቶቻቸውም፡ ለብቻቸው፤
14የቀሩት፡ወገኖች፡ዅሉ፡እያንዳንዱ፡ወገን፡ለብቻው፥ሴቶቻቸውም፡ለብቻቸው፡ያለቅሳሉ።