1በዚያ፡ቀን፡ለዳዊት፡ቤትና፡በኢየሩሳሌም፡ለሚኖሩ፡ከኀጢአትና፡ከርኵሰት፡የሚያነጻ፡ምንጭ፡ይከፈታል።
2በዚያ፡ቀን፥ይላል፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፥የጣዖታትን፡ስም፡ከምድር፡አጠፋለኹ፥ከዚያም፡በዃላ፡ አይታሰቡም፤ደግሞም፡ሐሰተኛዎችን፡ነቢያትና፡ርኩስ፡መንፈስን፡ከምድር፡ላይ፡አስወግዳለኹ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
3ማንም፡ደግሞ፡ትንቢት፡ቢናገር፡የወለዱት፡አባቱና፡እናቱ፦አንተ፡በእግዚአብሔር፡ስም፡ሐሰትን፡ ተናግረኻልና፥በሕይወት፡አትኖርም፡ይሉታል፤ትንቢትንም፡ሲናገር፡የወለዱት፡አባቱና፡እናቱ፡ይወጉታል።
4በዚያም፡ቀን፡ነቢያቱ፡ዅሉ፡ትንቢትን፡ሲናገሩ፡እያንዳንዱ፡ስለ፡ራእዩ፡ያፍራል፤ያታልሉም፡ዘንድ፡ የማቅ፡ልብስ፡አይለብሱም።
5ርሱ፡ግን፦ከታናሽነቴ፡ዠምሮ፡ባሪያ፡ኾኜ፡ነበርኹና፡ገበሬ፡ሰው፡ነኝ፡እንጂ፡ነቢይ፡አይደለኹም፡ ይላል።
6ሰውም፦ይህ፡በእጅኽ፡መካከል፡ያለ፡ቍስል፡ምንድር፡ነው፧ይለዋል።ርሱም፦በወዳጆቼ፡ቤት፡ የቈሰልኹት፡ቍስል፡ነው፡ይላል።
7ሰይፍ፡ሆይ፥ባልንጀራዬ፡በኾነው፡ሰው፡በእረኛዬ፡ላይ፡ንቃ፥ይላል፡የሰራዊት፡ጌታ፡ እግዚአብሔር፤እረኛውን፡ምታ፥በጎቹም፡ይበተናሉ፤እጄንም፡በታናናሾች፡ላይ፡እመልሳለኹ።
8በምድርም፡ዅሉ፡ላይ፡ኹለት፡ክፍል፡ተቈርጠው፡ይሞታሉ፥ይላል፡እግዚአብሔር፤ሦስተኛውም፡ክፍል፡ በርሷ፡ውስጥ፡ይቀራል።
9ሦስተኛውንም፡ክፍል፡ወደ፡እሳት፡አገባለኹ፥ብርም፡እንደሚነጥር፡አነጥራቸዋለኹ፥ወርቅም፡እንደሚፈተን፡ እፈትናቸዋለኹ፤እነርሱም፡ስሜን፡ይጠራሉ፥እኔም፡እሰማቸዋለኹ፤እኔም፦ይህ፡ሕዝቤ፡ነው፡ እላለኹ፤ርሱም፦እግዚአብሔር፡አምላኬ፡ነው፡ይላል።