Skip to content
← Zechariah

Chapter 2 · Amharic

Zechariah

1ዐይኖቼንም፡አነሣኹ፤እንሆም፥በእጁ፡የመለኪያ፡ገመድ፡የያዘ፡አንድ፡ሰውን፡አየኹ።

2እኔም፦አንተ፡ወዴት፡ትኼዳለኽ፧አልኹ።ርሱም፦የኢየሩሳሌምን፡ወርድና፡ርዝመት፡ስንት፡መኾኑን፡ ሰፍሬ፡አይ፡ዘንድ፡እኼዳለኹ፡አለኝ።

3እንሆም፥ከእኔ፡ጋራ፡ይነጋገር፡የነበረው፡መልአክ፡ወጣ፥ሌላም፡መልአክ፡ሊገናኘው፡ወጣ፥

4እንዲህም፡አለው፦ሩጥ፥ይህንም፡ጕልማሳ፡እንዲህ፡በለው፦ኢየሩሳሌም፡በውስጧ፡ካሉት፡ሰዎችና፡ እንስሳዎች፡ብዛት፡የተነሣ፡ቅጥር፡እንደሌላቸው፡መንደሮች፡ኾና፡ትኖራለች።

5እኔ፡በዙሪያዋ፡የእሳት፡ቅጥር፡እኾንላታለኹ፥በውስጧም፡ክብርን፡እኾናለኹ፥ይላል፡እግዚአብሔር።

6እናንተ፡ሆይ፥ከሰሜን፡ምድር፡ሽሹ፥ይላል፡እግዚአብሔር፤እንደ፡አራቱ፡የሰማይ፡ነፍሳት፡ በትኛችዃለኹና፥ይላል፡እግዚአብሔር።

7አንቺ፡ከባቢሎን፡ሴት፡ልጅ፡ጋራ፡የምትኖሪ፡ጽዮን፡ሆይ፥ኰብልዪ።

8የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላልና፦ከክብሩ፡በዃላ፡ወደበዘበዟችኹ፡አሕዛብ፡ ልኮኛል፤የሚነካችኹ፡የዐይኑን፡ብሌን፡የሚነካ፡ነውና።

9እንሆ፥እጄን፡በላያቸው፡አወዛውዛለኹ፥ተገዝተው፡ለነበሩት፡ብዝበዛ፡ይኾናሉ፤የሰራዊት፡ጌታ፡ እግዚአብሔርም፡እንደ፡ላከኝ፡ታውቃላችኹ።

10የጽዮን፡ልጅ፡ሆይ፥እንሆ፥መጥቼ፡በመካከልሽ፡እኖራለኹና፡ዘምሪ፥ደስም፡ይበልሽ፥ይላል፡ እግዚአብሔር።

11በዚያም፡ቀን፡ብዙ፡አሕዛብ፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ይጠጋሉ፥ሕዝብም፡ይኾኑኛል፤በመካከልሽም፡ እኖራለኹ፥የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔርም፡ወደ፡አንቺ፡እንደ፡ላከኝ፡ታውቂያለሽ።

12እግዚአብሔርም፡ይሁዳን፡ዕድል፡ፈንታው፡አድርጎ፡በተቀደሰችው፡ምድር፡ይወርሰዋል፥ኢየሩሳሌምንም፡ ዳግመኛ፡ይመርጣል።

13እግዚአብሔር፡ከተቀደሰ፡ማደሪያው፡ነቅቷልና፥ሥጋ፡ለባሽ፡ዅሉ፡ሆይ፥በፊቱ፡ዝም፡በል።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source