1ርሱም፡ታላቁን፡ካህን፡ኢያሱን፡በእግዚአብሔር፡መልአክ፡ፊት፡ቆሞ፡አሳየኝ፥ሰይጣንም፡ይከሰ፟ው፡ዘንድ፡ በስተቀኙ፡ቆሞ፡ነበር።
2እግዚአብሔርም፡ሰይጣንን፦ሰይጣን፡ሆይ፥እግዚአብሔር፡ይገሥጽኽ፤ኢየሩሳሌምን፡የመረጠ፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org እግዚአብሔር፡ይገሥጽኽ፤በእውኑ፡ይህ፡ከእሳት፡የተነጠቀ፡ትንታግ፡አይደለምን፧አለው።
3ኢያሱም፡እድፋም፡ልብስ፡ለብሶ፡በመልአኩ፡ፊት፡ቆሞ፡ነበር።ርሱም፡መልሶ፡በፊቱ፡ የቆሙትን፦እድፋሙን፡ልብስ፡ከርሱ፡ላይ፡አውልቁ፡አላቸው።ርሱንም፦እንሆ፥አበሳኽን፡ከአንተ፡ አርቄያለኹ፥ጥሩ፡ልብስም፡አለብስኻለኹ፡አለው።
5ደግሞ፦ንጹሕ፡ጥምጥም፡በራሱ፡ላይ፡አድርጉ፡አለ።እነርሱም፡በራሱ፡ላይ፡ንጹሕ፡ጥምጥም፡ አደረጉ፥ልብስንም፡አለበሱት፤የእግዚአብሔርም፡መልአክ፡በአጠገቡ፡ቆሞ፡ነበር።
6የእግዚአብሔርም፡መልአክ፡በኢያሱ፡እንዲህ፡ሲል፡አዳኘበት።
7የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦በመንገዴ፡ብትኼድ፡ትእዛዜንም፡ብትጠብቅ፥በቤቴ፡ላይ፡ ትፈርዳለኽ፥አደባባዮቼንም፡ትጠብቃለኽ፥በዚህም፡ከቆሙት፡ከነዚህ፡ጋራ፡መግባትን፡እሰጣለኹ።
8ታላቁ፡ካህን፡ኢያሱ፡ሆይ፥ስማ፤በፊትኽም፡የሚቀመጡት፡ባልንጀራዎችኽ፡ለምልክት፡የሚኾኑ፡ሰዎች፡ ናቸውና፥ይስሙ፤እንሆ፥እኔ፡ባሪያዬን፡ቍጥቋጥ፡አወጣለኹ።
9በኢያሱ፡ፊት፡ያኖርኹት፡ድንጋይ፥እንሆ፥አለ፤በአንዱ፡ድንጋይ፡ላይ፡ሰባት፡ዐይኖች፡ አሉ፤እንሆ፥ቅርጹን፡እቀርጻለኹ፥ይላል፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፥የዚያችንም፡ምድር፡በደል፡ባንድ፡ ቀን፡አስወግዳለኹ።
10በዚያ፡ቀን፥ይላል፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፥እያንዳንዱ፡ከወይኑና፡ከበለሱ፡በታች፡ኾኖ፡ ባልንጀራውን፡ይጠራል።