1ከእኔም፡ጋራ፡ይነጋገር፡የነበረው፡መልአክ፡ተመልሶ፡ከእንቅልፉ፡እንደሚነቃ፡ሰው፡አነቃኝ።
2ርሱም፦የምታየው፡ምንድር፡ነው፧አለኝ።እኔም፦እንሆ፥ዅለንተናው፡ወርቅ፡የኾነውን፡መቅረዝ፡ አየኹ፤የዘይትም፡ማሰሮ፡በራሱ፡ላይ፡ነበረ፥ሰባትም፡መብራቶች፡ነበሩበት፤በራሱም፡ላይ፡ለነበሩት፡ መብራቶች፡ሰባት፡ቧንቧዎች፡ነበሯቸው።
3ኹለት፡የወይራ፡ዛፎች፥አንዱ፡በማሰሮው፡በስተቀኝ፡አንዱም፡በስተግራው፡ኾነው፥በአጠገቡ፡ነበሩ፡ አልኹ።
4ከእኔ፡ጋራ፡ይነጋገር፡ለነበረውም፡መልአክ፡መልሼ፦ጌታዬ፡ሆይ፥እነዚህ፡ምንድር፡ናቸው፧አልኹት።
5ከእኔ፡ጋራ፡ይነጋገር፡የነበረውም፡መልአክ፡መልሶ፦እነዚህ፡ምን፡እንደ፡ኾኑ፡ አታውቅምን፧አለኝ።እኔም፦ጌታዬ፡ሆይ፥አላውቅም፡አልኹ።
6መልሶም፦ለዘሩባቤል፡የተባለው፡የእግዚአብሔር፡ቃል፡ይህ፡ነው፦በመንፈሴ፡እንጂ፡በኀይልና፡ በብርታት፡አይደለም፥ይላል፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር።
7ታላቅ፡ተራራ፡ሆይ፥አንተ፡ምንድር፡ነኽ፧በዘሩባቤል፡ፊት፡ደልዳላ፡ሜዳ፡ ትኾናለኽ፤ሰዎችም፦ሞገስ፥ሞገስ፡ይኹንለት፡ብለው፡እየጮኹ፡ርሱ፡መደምደሚያውን፡ድንጋይ፡ያወጣል፡ ብሎ፡ተናገረኝ።
8የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
9የዘሩባቤል፡እጆች፡ይህን፡ቤት፡መሠረቱ፥የርሱም፡እጆች፡ይፈጽሙታል፤የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔርም፡ ወደ፡እናንተ፡እንደ፡ላከኝ፡ታውቃላችኹ።
10የጥቂቱን፡ነገር፡ቀን፡የናቀ፡ማን፡ነው፧እነዚህ፡ሰባቱ፡ደስ፡ብሏቸው፡በዘሩባቤል፡እጅ፡ቱንቢውን፡ ያያሉ፤እነዚህም፡በምድር፡ዅሉ፡የሚዘዋወሩ፡የእግዚአብሔር፡ዐይኖች፡ናቸው።
11እኔም፡መልሼ፦በመቅረዙ፡በስተቀኝና፡በስተግራ፡ያሉ፡እነዚህ፡ኹለት፡የወይራ፡ዛፎች፡ምንድር፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ናቸው፧አልኹት።
12ኹለተኛም፡መልሼ፦በኹለቱ፡የወርቅ፡ቧንቧዎች፡አጠገብ፡ኾነው፡የወርቁን፡ዘይት፡የሚያፈሱ፟፡እነዚህ፡ ኹለት፡የወይራ፡ቅርንጫፎች፡ምንድር፡ናቸው፧አልኹት።
13ርሱም፡መልሶ፦እነዚህ፡ምን፡እንደ፡ኾኑ፡አታውቅምን፧አለኝ።እኔም፦ጌታዬ፡ሆይ፥አላውቅም፡ አልኹት።
14ርሱም፦በምድር፡ዅሉ፡ጌታ፡አጠገብ፡የቆሙት፡ኹለቱ፡የተቀቡት፡እነዚህ፡ናቸው፡አለኝ።