Skip to content
← Zechariah

Chapter 6 · Amharic

Zechariah

1ተመልሼም፡ዐይኖቼን፡አነሣኹ፥እንሆም፥አራት፡ሠረገላዎች፡ከኹለት፡ተራራ፡መካከል፡ሲወጡ፡ አየኹ፤ተራራዎቹም፡የናስ፡ተራራዎች፡ነበሩ።

2በፊተኛው፡ሠረገላ፡መጋላ፡ፈረሶች፥በኹለተኛውም፡ሠረገላ፡ዱሪ፡ፈረሶች፡ነበሩ፥

3በሦስተኛውም፡ሠረገላ፡ዐምባላይ፡ፈረሶች፥በአራተኛውም፡ሠረገላ፡ቅጥልጣል፡ፈረሶች፡ነበሩ።

4ከእኔ፡ጋራ፡ይነጋገር፡ለነበረውም፡መልአክ፡መልሼ፦ጌታዬ፡ሆይ፥እነዚህ፡ምንድር፡ናቸው፧አልኹት። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

5መልአኩም፡መልሶ፦እነዚህ፡በምድር፡ዅሉ፡ጌታ፡ፊት፡ከቆሙበት፡ስፍራ፡የሚወጡ፡አራቱ፡የሰማይ፡ ነፋሳት፡ናቸው።

6ዱሪ፡ፈረሶች፡ያሉበት፡ወደ፡ሰሜን፡ይወጣል፤ዐምባላዮቹም፡ከነርሱ፡በዃላ፡ይወጣሉ፥ቅጥልጣሎችም፡ ወደ፡ደቡብ፡ይወጣሉ፡አለኝ።

7መጋላዎቹም፡ደግሞ፡ወጡ፡በምድርም፡ይመላለሱ፡ዘንድ፡ለመኼድ፡ይፈልጉ፡ ነበር፤ርሱም፦ኺዱ፥በምድር፡ላይ፡ተመላለሱ፡አለ።እነርሱም፡በምድር፡ላይ፡ተመላለሱ።

8ጮኾም፦እንሆ፥ወደሰሜን፡ምድር፡የሚወጡት፡እነርሱ፡መንፈሴን፡በሰሜን፡ምድር፡ላይ፡አሳርፈዋል፡ ብሎ፡ተናገረኝ።

9የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦

10ከባቢሎን፡ከመጡት፡ምርኮኛዎች፡ከሔልዳይና፡ከጦብያ፡ከዮዳዔም፡ውሰድ፤በዚያም፡ቀን፡መጥተኽ፡ ወደሶፎንያስ፡ልጅ፡ወደኢዮስያስ፡ቤት፡ግባ።

11ብርንና፡ወርቅን፡ከነርሱ፡ውሰድ፥አክሊሎችንም፡ሥራ፤በታላቁም፡ካህን፡በኢዮሴዴቅ፡ልጅ፡በኢያሱ፡ራስ፡ ላይ፡ድፋቸው፥

12እንዲህም፡በለው፦የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥ስሙ፡ቍጥቋጥ፡የሚባል፡ ሰው፡በስፍራው፡ይበቅላል፥የእግዚአብሔርንም፡መቅደስ፡ይሠራል።

13ርሱ፡የእግዚአብሔርን፡መቅደስ፡ይሠራል፥ክብርንም፡ይሸከማል፥በዙፋኑም፡ላይ፡ተቀምጦ፡ ይነግሣል፤በዙፋኑም፡ላይ፡ካህን፡ይኾናል፥የሰላምም፡ምክር፡በኹለቱ፡መካከል፡ይኾናል።

14አክሊሎችም፡ለሔሌምና፡ለጦብያ፡ለዮዳዔም፡ለሶፎንያስም፡ልጅ፡ለሔን፡በእግዚአብሔር፡መቅደስ፡ውስጥ፡ ለመታሰቢያ፡ይኾናሉ።

15በሩቅም፡ያሉት፡መጥተው፡የእግዚአብሔርን፡መቅደስ፡ይሠራሉ፤የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔርም፡ወደ፡ እናንተ፡እንደ፡ላከኝ፡ታውቃላችኹ።የአምላካችኹንም፡የእግዚአብሔርን፡ቃል፡አጥብቃችኹ፡ብትሰሙ፡ይህ፡ ይኾናል።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source