1በንጉሡም፡በዳርዮስ፡በአራተኛው፡ዓመት፡ካሴሉ፡በሚባል፡በዘጠነኛው፡ወር፡በአራተኛው፡ቀን፡ የእግዚአብሔር፡ቃል፡ወደ፡ዘካርያስ፡መጣ።
2የቤቴልም፡ሰዎች፡ሳራሳርንና፡ሬጌሜሌክን፡ሰዎቻቸውንም፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ይለምኑ፡ዘንድ፥
3ለሰራዊት፡ጌታ፡ለእግዚአብሔር፡ቤት፡ካህናት፡ለነቢያትም፦ባለፉት፡ዓመታት፡እንዳደረግኹት፡ በዐምስተኛው፡ወር፡መለየትና፡ማልቀስ፡ይገ፟ባ፟ኛልን፧ብለው፡ይናገሩ፡ዘንድ፡ልኳቸው፡ነበር።
4የሰራዊትም፡ጌታ፡የእግዚአብሔር፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
5ለምድሩ፡ሕዝብ፡ዅሉ፡ለካህናትም፡እንዲህ፡ብለኽ፡ተናገራቸው፦በዚህ፡በሰባው፡ዓመት፡በዐምስተኛውና፡ በሰባተኛው፡ወር፡በጾማችኹና፡ባለቀሳችኹ፡ጊዜ፥በእውኑ፡ለእኔ፡ጾም፡ጾማችኹልኝ፧
6በምትበሉበትና፡በምትጠጡበትስ፡ጊዜ፥ለራሳችኹ፡የምትበሉና፡የምትጠጡ፡አይደላችኹምን፧
7ኢየሩሳሌምና፡በዙሪያዋ፡ያሉ፡ከተማዎች፡ገና፡ሰዎች፡ባሉባቸው፡ጊዜ፥በምቾትም፡ተቀምጠው፡ ሳሉ፥ደቡቡና፡ቈላውም፡ሰዎች፡ባሉባቸው፡ጊዜ፥እግዚአብሔር፡በቀደሙት፡ነቢያት፡እጅ፡የተናገረውን፡ቃል፡ መስማት፡አይገ፟ባ፟ችኹምን፧
8የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡ዘካርያስ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
9የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ብሎ፡ተናግሯል፦እውነተኛውን፡ፍርድ፡ፍረዱ፤ቸርነትንና፡ ምሕረትን፡ዅላችኹ፡ለወንድሞቻችኹ፡አድርጉ፤
10መበለቲቱንና፡ድኻ፡አደጉን፥መጻተኛውንና፡ችግረኛውን፡አትበድሉ፤ከእናንተም፡ማንም፡በወንድሙ፡ ላይ፡ክፉውን፡ነገር፡በልቡ፡አያስብ።
11እነርሱ፡ግን፡ደንደሳቸውን፡አዞሩ፡እንጂ፡መስማትን፡እምቢ፡አሉ፤እንዳይሰሙም፡ዦሯቸውን፡አደነቈሩ።
12የሰራዊትም፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡በቀደሙት፡ነቢያት፡እጅ፡በመንፈሱ፡የላከውን፡ሕጉንና፡ቃሉን፡ እንዳይሰሙ፡ልባቸውን፡እንደ፡አልማዝ፡አጠነከሩ፤ስለዚህ፥ከሰራዊት፡ጌታ፡ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ታላቅ፡ ቍጣ፡መጣ።
13እኔ፡በጠራኹ፡ጊዜ፡እነርሱ፡እንዳልሰሙኝ፥እንዲሁ፡እነርሱ፡በሚጠሩበት፡ጊዜ፡እኔ፡አልሰማም፥ይላል፡ የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፤
14ወደማያውቋቸውም፡አሕዛብ፡ዅሉ፡በዐውሎ፡ነፋስ፡በተንዃቸው።እንዲሁ፡ከነርሱ፡በዃላ፡ምድሪቱ፡ ባድማ፡ኾናለች፥የሚተላለፍባትና፡የሚመላለስባትም፡አልነበረም፤ያማረችውንም፡ምድር፡ባድማ፡አደረጓት።